ለመጀመሪያ ጊዜ ከቻይና ውጭ የሚገኙ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ቻይና ከሚገኙት በልጧል
ለመጀመሪያ ጊዜ ከቻይና ውጭ የሚገኙ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ቻይና ከሚገኙት በልጧል
በዓለማቀፍ ደረጃ እስከ ዛሬ መጋቢት 07 ቀን 2012 ዓ.ም ጧት 167,457ተጠቂዎች ሲገኙ ከዚህም ከ 86,400 በላይ የሚሆኑት ከቻይና ውጭ ለቫይረሱ በተጋለጡ ሀገራት የሚገኙ ናቸው፡፡ ከቻይና ውጭ ከ3170 በላይ ሞትም ተመዝግቧል፡፡
በቻይና የተለዩ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ደግሞ ከ 81,000 በላይ ሲሆን ከ3,200 በላይ የሚሆኑት ሲሞቱ ከ67,800 በላይ ታማሚዎች አገግመው ከሆስፒታል እንደወጡ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
65 ሰዎች ሞተውባት የተጠቂዎቿ ቁጥር ከ 3,400 የዘለለባት ዩ.ኤስ አሜሪካ ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አውጃለች፡፡
የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በርካታ የአፍሪካ ሀገራትም ጠንካራ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምረዋል፡፡ የምስራቅ አፍሪካዎቹን ኬኒያና ጅቡቲን ጨምሮ በትንሹ 10 ሀገራት ዓለም አቀፍ በረራዎችን በከፊል አሊያም ሙሉ በሙሉ ለጊዜው አግደዋል፡፡
ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል መደረግ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች እናስታውስዎ!