ኮሮና “ሰው ሰራሽም አይደለም፣ ላቦራቶሪ ውስጥም አልተሰራም”- ባለሙያዎች
የአለም ጤና ድርጅት ቃል-አቀባይ ፋደል ችያብ ቫይረሱ በላቦራቶሪ የተሰራ ነው የሚሉትን ትንታኔዎች አጣጥለዋል
ሳይንቲስቶች ኮሮና ቫይረስ በተፈጥሮ የተከሰተ ነው የሚለውን እምነታቸውን አጠናክረዋል
ሳይንቲስቶች ኮሮና ቫይረስ በተፈጥሮ የተከሰተ ነው የሚለውን እምነታቸውን አጠናክረዋል
የኮሮና ቫይረስ መነሻ ምክያት እያወዛገበ ባለበት ሰአት ሳይንቲስቶች ሳርስ ኮቪድ 2 ወይም ኮሮና ቫይረስ የመጣው ከተፈጥሮ ነው የሚለውን እምነታቸውን ማጠናከራቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በኮሎቢያ ዩኒቨርሲቲ የማይክሮ ባዮሎጅ ፕሮፌሰር የሆኑት ቪንሰንት ራሴኒሎ በቅርብ በዲያሎግ ላይ በነበራቸው ቃለመጠይቅ ቫይረሱ በሰውም አልተሰራም፤ ላቦራቶሪ ውስጥም አልተፈጠረም ብለዋል፡፡ ቫይረሱ የባዮሎጂ ጦር መሳሪያም አይደለም ሲሉ ፕሮፌሰሩ አብራርተዋል፡፡
ፕሮፌሰሩ ቫይረሱ ከተፈጥሮ የመጣ ነው፤ እንደዚህ አይነት ባህሪይ ያለው ቫይረስ ተፈጥሮ ብቻ ነች መስራት የምትችለው ብለዋል፡፡
ቫይረሱ በተፈጥሮ የመከሰቱ ነገር ምንም ጥያቄ የለውም ያሉት ፕሮፌሰሩ ከዚህ ውጭ የሚያስቡት ሳይንስን የማያዩ ናቸው ብለዋል፡፡
የአለም ጤና ድርጅት ቃል-አቀባይ ፋደል ችያብ ሁሉም ጥናቶች የሚያሳዩት ቫይረሱ ምንጩ ከእንሰሳት መሆኑን ነው በማለት ቫይረሱ በላቦራቶሪ የተሰራ ነው የሚሉትን ትንታኔዎች አጣጥለዋል፤ ቫይረሱ በሌሊት ወፍ ውስጥ ሊኖር የሚችልበት ሰፊ እድል መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡
ፕሮፌሰር ራሴኒሎ ጨምረው እንደገለጹት የቫይረሱ ምንጭ የሌሊት መሆኗ ቢታወቅም፣ ቫይረሱ ከሌሊት ወፍ ቀጥታ ወደ ሰው ይተላለፍ እንደሆነ ወይንም በመሀል ሌላ አንሰሳ መኖሩ ግን እንደማይታወቅ ገልጸዋል፡፡ ቫይረሱን ከሌሊት ወፍ ወደ ሰው የሚያስተላልፍ ሌላ እንሰሳ ይኑር አይኑር ለማወቅ ሰፊ ጥናት እንደሚያስፈልግ ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም እንደፕሮፌሰሩ ገለፃ የቫይረሱን ምንጭ ማወቅ ወደፊት ሌላ ወረርሽኝ እንዳይከሰት ይረዳል ብለዋል፡፡
በሎንዶን ዙኦሎጂካል ሶሳይቲ፣የዙኦሎጂ ኢንስትቲዩት ዳይሬክትር የሆኑት ከሌሎች ቫይረሶች እንደምንማረው ከሆነ ቫይረሱን ወደ ሰው ለማስተላለፍ በመሀል አስተላላፊ የሚኖርበት እድል አለ ብለዋል፡፡
ከቻይና ውሀን ግዛት የተቀሰቀሰው ኮሮና ቫይረስ መላውን አለም አዳርሶ ወደ 300ሺ የሚጠጉ ሰዎችን ለህልፈተ ሂወት ሲዳርግ፤ከ3 ሚሊዮን በላይ የሆኑ ሰዎች ደግሞ አጥቅቷል፡፡