በውሀን ሆስፒታል ውስጥ የነበሩ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች በሙሉ ወጡ
ዜጎች ሁለተኛ ወረርሽኝ ይመጣል እያሉ ይሰጋሉ፤የንግድ ተቋማትም በእግራቸው ለመቆም እየታገሉ ነው
በቻይና ዉሀን የነበሩ የኮሮና ቫይረስ ተማሚዎች ሙሉ በሙሉ አገግመው ወጡ
በቻይና ዉሀን የነበሩ የኮሮና ቫይረስ ተማሚዎች ሙሉ በሙሉ አገግመው ወጡ
በቻይና ውሀን ከተማ ሆስፒታል ውስጥ የነበሩ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ሙሉ በሙሉ አገግመው መውጣታቸውን የብሔራዊ የጤና ኮሚሽን ቃል አቀባይ ሚ ፌንግ አስታውቀዋል፡፡
ሚ እንደገለጹት ከውሀንና ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች ባደረጉት ጥረት ሁሉም የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች በትናንትናው እለት ድነው ከሆስፒታል ወጥተዋል፡፡
ውሀን በቫይረሱ ምክንያት የእንቅስቃሴ እግድ የጣለች የመጀመሪያዋ ሀገር ነች፤ ከወራት ፍርሀትና አለመረጋጋት በኋላ ቀስ እያለች ወደ መደበኛ ሁኔታ እየተመለሰች ነው፡፡
ነገርግን ከተማዋንና ሁቤ ግዛትን ለ76 ቀናት እንዲዘጉ ያደረጋቸው የወረርሽኙ ጠባሳ ከመሬት በታች አለ፡፡ ብዙ ዜጎች ሁለተኛ ወረርሽኝ ይመጣል እያሉ ይሰጋሉ፤የንግድ ተቋማትም በእግራቸው ለመቆም እየታገሉ ይገኛሉ፡፡
ኮሮና ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀሰቀሰው ባለፈው ታህሳስ ወር በቻይናዋ ዉሀን ከተማ ነበር፡፡ቫይረሱ ከተከሰተ ከሳምንታት በኋላ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ጨመረ መንግስትም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በማሰብ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥሎም ነበር፡፡
ምንምእንኳን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጥረት ቢደረግም፣ ቫይረሱ መላውን አለም አዳርሶ ከ200ሺ በላይ ሰዎች እንዲሞቱ ምክንያት ሆኗል፤ ቁጥራቸው ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን አጥቅቷል፡፡