በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ዓለማቀፍ ወረርሽኝ የሆነው ኮሮና ቫይረስ ከ1,000,000 በላይ ህዝብ አጥቅቷል
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ዓለማቀፍ ወረርሽኝ የሆነው ኮሮና ቫይረስ ከ1,000,000 በላይ ህዝብ አጥቅቷል
የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቭረሲቲ መረጃ እንደሚያሳየው የዛሬ አንድ ወር፣ የካቲት 25፣ በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ 92,000 ያክል ሰዎች ብቻ የነበሩ ሲሆን ከነዚህም ከ80,000 በላዩ ቻይናውያን ናቸው፡፡
ባለፈው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የተጠቂዎች ቁጥር በፍጥነት ተተኩሶ ዛሬ፣ መጋቢት 25፣ ከ1,017,000 በላይ ህዝብ በቫይረሱ ተይዟል፡፡
የካቲት 25 (ከወር በፊት) 118 ብቻ ታማሚዎች የነበሯት አሜሪካ ዛሪ ላይ በቫይረሱ የተያዙ ዜጎቿ ከ245,000 በላይ ናቸው፡፡ በዚህም በከፍተኛ ልዩነት በተጠቂዎች ቁጥር ዓለምን የምትመራ ሲሆን ከ6,000 በላይ ሰዎች ሞተውባታል፡፡ ሀገሪቱ የመጀመሪውን ሞት ያስመዘገበችው የካቲት 22 ነበር፡፡
የወረርሽኙ ከፍተኛ የጉዳት ጫፍ እና ማብቂያው መች እንደሚሆን መተንበይ አይቻልም፡፡
እንደ ደቡብ ኮሪያ እና ቻይና ያሉ አንዳንድ ሀገራት የቫይረሱን ስርጭት በመቆጣጠር ላይ ቢሆኑም በሌሎች ሀገራት ግን በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑ አሳሳቢነቱን ከፍ ያደርገዋል፡፡
እስካሁን አሜሪከ፣ ጣሊያን እና ስፔን ከ100,000 በላይ ታማሚዎች የሚገኙባቸው ግንባር ቀደም ቫይረሱ የተሰራ ጨባቸው ሀገራት ናቸው፡፡
አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ከ53000 በላይ ሲደርስ 14,000 የሚሆኑ ሟቾች ከጣሊያን ናቸው፡፡ ስፔን ደግሞ ከ10,000 በላይ ሞት አስመዝግባለች፡፡
85,000 ያክል ታማሚዎች የተገኙባት ጀርመንም በታማሚዎች ቁጥር ከቻይና በልጣለች፡፡ ሀገሪቱ ከ1,000 በላይ ዜጎቿ የሞቱባት ሲሆን የሟቾቹ ቁጥር ከፍ እያለ እንደሚሄድ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡- ሲኤንኤን