በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ ሚሊዮን ይደርሳል-የዓለም ጤና ድርጅት
በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ባለበት ወቅት ለድሀ ሀገራት የወለድ ስረዛ ያስፈልጋል-ዶ/ር ቴድሮስ
በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ ሚሊዮን ይደርሳል-የአለም ጤና ድርጅት
በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ ሚሊዮን ይደርሳል-የአለም ጤና ድርጅት
የአለም ጤና ድርጅት ኃላፊ በአለም ላይ በፍጥነት ተስፋፍቶ 205 ሀገራትን ያዳረሰው የኮሮና ቫይረስ/ ኮቪድ 19 እጅጉን እንደሚሳስባቸው እየገለጹ ነው፡፡
የድርጅቱ ዳሬክተር ጄነራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም የአለም ጤና ድርጅት፣የአለም ባንክና የአለምአቀፉ ሞናተሪ ፈንድ ታዳጊ ሀገራት የኮሮና ቫይረስን ማህበራዊና ኢከኖሚያዊ ተጽእኖ መቋቋም እንዲችሉ የብድር ወለድ ስረዛ ድጋፍ ያደርጋሉ ብለዋል፡፡
ዶ/ር ቴድሮስ “ባለፉት 5 ሳምንታት የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር እጅጉን ያሻቀበ ሲሆን የሞቱት ሰዎች ቁጥር ደግሞ በእጥፍ አድጓል” ብለዋል፡፡
የአለም ጤና ድርጅት ዳሬክተር ጄነራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም በአለም አቀፍ ደረጃ “በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ደግሞ 50,000 ይደርሳል” ብለዋል፡፡
በየካቲት ወር ወደ ቻይና የሄደው ቡድን አባል የነበሩት የአለምጤና ድርጅት ኢፒዲሞሎጂስት ዶ/ር ማሪያ ቫን ከርኮቬ ስለኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ልዩነት ተጠይቀው በአለምጤና ድርጅት ትርጉም መሰረት በላብራቶሪ የተጋገጠ ሲሆን ቫይረሱ መኖሩ ሚረጋገጠው ብለዋል፡፡
ወረርሽኙ እየተስፋፋ ያለው ትኩሳትና ሳል ጨምሮ የበሽታውን ምልክት ባሳዩ ሰዎች ሰለሆነ ድርጅቱ የበሽታውን አጠቃላይ ሁኔታ መረዳት አለበት ብለዋል ዶ/ር ቫን ከርኮቬ፡፡
ዶ/ር ቴድሮስ፣ ህንድ ባለፈው ሳምንት ለ21 ቀናት የሚቆይ የእንቅስቃሴ እግድ ከጣለች በኋላ የ22 ቢሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ ማነቃቂያ በመመደብ 800 ሚሊዮን ለሚሆኑ ደሀ ህንዳዉያን ምግብ ለማቅረብና ለ204 ሚሊዮን ሴቶች የገንዘብ ድጎማ ለማድረግ ያሳለፈችውን ውሳኔ አድንቀዋል፡፡
ብዙ ታዳጊ ሀገራት የማህበረሰባዊ ደህንነትን ለመተግበር እየታገሉ መሆኑን ኃፊው አስታውቀዋል፡፡
ዶ/ር ቴድሮስ የወለድ ስርዛ ድጋፍ ረጅም ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም በተፋጠኑ ሁኔታ ይህን ማድረግ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኮሮና ቫይረስ እስካሁን 48,580 ለሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን የወርልዶሜትር መረጃ ያሳያል፡፡ እንደወርልዶሜትር መረጃ ከሆነ እስካሁን 955,412 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 203,013 ሰዎች አገግመው ከቫይረሱ ነፃ ሆነዋል፡፡