ባጠቃላይ በ198 ሀገራት 493,520 ሰዎች ተጠቅተው ከ22,300 በላይ ሰዎች ሞተዋል
ባጠቃላይ በ198 ሀገራት 493,520 ሰዎች ተጠቅተው ከ22,300 በላይ ሰዎች ሞተዋል
በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ 7 ቀዳሚ ሀገራት
ቻይና፡- የተጠቁ ሰዎች ቁጥር፡ 81,285 የሞቱ፡ 3,287 ያገገሙ፡ 74,051
ጣልያን፡- የተጠቁ ሰዎች ቁጥር፡ 74,386 የሞቱ፡ 7,503 ያገገሙ፡ 9,362
ዩኤስ አሜሪካ፡- የተጠቁ ሰዎች ቁጥር፡ 68,594 የሞቱ፡ 1,032 ያገገሙ፡ 394
ስፔን፡- የተጠቁ ሰዎች ቁጥር፡ 56,188 የሞቱ፡ 4,089 ያገገሙ፡ 5,367
ጀርመን፡- የተጠቁ ሰዎች ቁጥር፡ 39,502 የሞቱ፡ 222 ያገገሙ፡ 3,547
ኢራን፡- የተጠቁ ሰዎች ቁጥር፡ 29,406 የሞቱ፡ 2,234 ያገገሙ፡ 9,625
ፈረንሳይ፡- የተጠቁ ሰዎች ቁጥር፡ 25,233 የሞቱ፡ 1,331 ያገገሙ፡ 3,900
ባጠቃላይ በ198 ሀገራት ከ493,520 ሰዎች ተጠቅተው ከ22,300 በላይ ሰዎች ሲሞቱ 120 ሺ ገደማ ሰዎች አገግመዋል፡፡
በአፍሪካ የኮሮና ተጠቂዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው
ሀገራት (46) በጠቅላላው ሪፖርት የተደረጉ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች ቁጥር 2,819 ፣ 73 ሞት እና ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 211
በቀጣና ተከፍሎ ሲቀመጥ
ማዕከላዊ አፍሪካ (151 ተጠቂዎች ፣ 5 ሞት ፣ 3 ያገገሙ) ፡- ካሜሩን (75 ፣ 1 ፣ 2) ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፓብሊክ (5 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ቻድ (3 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ኮንጎ (4 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ (48 ፣ 3 ፣ 1) ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ (9 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ጋቦን (7 ፣ 1 ፣ 0)
ምስራቃዊ አፍሪካ (220 ተጠቂዎች ፣ 3 ሞት ፣ 5 ያገገሙ) :- ጅቡቲ (11 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ኤርትራ (4 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ኢትዮጵያ (12 ፣ 0 ፣ 4) ፣ ኬንያ (31 ፣ 0 ፣ 1) ፣ ማዳጋስካርካ (19 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሞሪሺየስ (63 ፣ 2 ፣ 0) ፣ ሩዋንዳ (41 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሲሸልስ (7 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሶማሊያ (2 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሱዳን (3 ፣ 1 ፣ 0) ፣ ታንዛኒያ (13 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ኡጋንዳ (14 ፣ 0 ፣ 0)
ሰሜናዊ አፍሪካ (1,159 ተጠቂዎች ፣ 53 ሞት ፣ 180 ያገገሙ) :- አልጄሪያ (302 ፣ 21 ፣ 77) ፣ ግብፅ (456 ፣ 21 ፣ 95) ፣ ሊቢያ (1 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሞሪታኒያ (2 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሞሮኮ (225 ፣ 6 ፣ 7) ፣ ቱኒዚያ (173 ፣ 5 ፣ 1)
ደቡባዊ አፍሪካ (747 ተጠቂዎች ፣ 1ሞት ፣ 2 ያገገሙ) :- አንጎላ (3 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ኢስዋቲኒ (5 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ሞዛምቢክ (5 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ናሚቢያ (6 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ደቡብ አፍሪካ (709 ፣ 0 ፣ 2) ፣ ዛምቢያ (16 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ዚምባብዌ (3 ፣ 1 ፣ 0)
ምዕራባዊ አፍሪካ (542 ተጠቂዎች ፣ 11 ሞት ፣ 21 ያገገሙ) :- ቤኒን (6 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ቡርኪና ፋሶ (146 ፣ 4 ፣ 5) ፣ ኬፕ ቨርዴ (3 ፣ 1 ፣ 0) ፣ ኮትዲቮር (80 ፣ 0 ፣ 3) ፣ ጋምቢያ (3 ፣ 1 ፣ 0) ፣ ጋና (105 ፣ 3 ፣ 1) ፣ ጊኒ (5 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ጊኒ-ቢሳዎ (2 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ላይቤሪያ (3 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ማሊ (2 ፣ 0 ፣ 0) ፣ ኒጀር (7 ፣ 1 ፣ 0) ፣ ናይጄሪያ (51 ፣ 1 ፣ 2) ፣ ሴኔጋል (105 ፣ 0 ፣ 9) ፣ ቶጎ (24 ፣ 0 ፣ 1) እንደሆነ የአፍሪካ የበሽታ ቁጥጥር ማእከል መረጃ ያሳያል፡፡
በአሜሪካ በ24 ሰዓታት ውስጥ 233 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሞቱ
ዩኤስ አሜሪካ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ትናንት ያስተናገደችው ሞት ከእስካሁኑ ትልቁ ሆኗል፡፡ በሀገሪቱ ቫይረሱ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን ተከትሎ ከአውሮፓ ቀጥሎ ሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ዋና ማእከል ልትሆን እንደምትችል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል፡፡
ጣሊያን አሁንም ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ ሞት ማስተናገዷን ቀጥላለች
በሟቾች ቁጥር በከፍተኛ ልዩነት እየመራች የምትገኘው ጣሊያን በትናንትናው እለት 683 ሰዎችን በቫይረሱ ስታጣ 5210 አዳዲስ ተጠቂዎችን አስመዝግባለች፡፡
የቡድን 20 አባል ሀገራት የዓለምን ምጣኔሃብት ለመታደግ 5 ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር መደቡ
የቀውስ ወቅት ስብሰባቸውን በቪደዮ ኮንፈረንስ ያደረጉት የቡድን 20 አባል ሃገራት መሪዎች የዓለም ምጣኔሃብት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሊደርስ ከሚችልበት ድቀት ለመታደግ የሚያስችል የ5 ትሪሊዮን ድጋፍ ለማድረግ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡መሪዎቹ ታዳጊ ሃገራትን ለመደገፍና መድኃኒቶችንና ክትባትን ለማዘጋጀት የሚደረጉ ጥረቶችን የዓለም የጤና ድርጅት በሚያቀርበው ምክረ ሃሳብ መሰረት ለማገዝም ቃል ገብተዋል፡፡
ሶስት ቢሊዮን ያክል ህዝብ በእገዳ ውስጥ እንዲቆይ ያስገደደው የኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር በመላው ዓለም ከ22 ሺ በላይ መድረሱ ይታወቃል፡፡
አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰው ወረርሽኙ የሚያስከትለው የኢኮኖሚ ቀውስ ከዚህ ቀደም ካጋጠሙ ከባድ የኢኮኖሚ ድቀቶች እጅግ ሊልቅ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡
በዩኤስ አሜሪካ እና ቻይና መካከል ግልጽ የሆነ መወነጃጀል ቢኖርም የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዓለም ከችግሩ ለመውጣት ከመወቃቀስ ይልቅ እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኮቪድ 19 የሰው ዘርን በሙሉ ስጋት ላይ ጥሏል ፣ በመሆኑም መላው የሰው ዘር ሊከላከለው ይገባል ሲሉ ጉተሬዝ ኮሮናን ለመከላከል ለድሀ ሀገራት የሚውል የ 2 ቢሊዮን ዶላር ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡