2 ተጨማሪ ጃፓናዊ እና 1 ኢትዮጵያዊ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል
ኮሮና ቫይረስ ከተገኘበት ጃፓናዊ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው 3 ሰዎች ቫይረሱ ተገኘባቸው
ከጃፓናዊው ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉ 117 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል ዛሬ መጋቢት 06 ቀን 2012 ዓ.ም 2 ጃፓናዊ እና 1 ኢትዮጵያዊ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ 4 ደርሰዋል አጠቃላይ ተጠቂዎች።
በአሁኑ ሰዓት የመጀመሪያው ታማሚ በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ሲሆን በለይቶ ህክምና መስጫ ማእከል ህክምና እየተደረገለት ነው ።