
ኢትዮጵያ ከቻይዋ ውሃን ግዛት የሚመጡ መንገደኞችን ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ወሰነች
ኢትዮጵያ ከቻይዋ ውሃን ግዛት የሚመጡ መንገደኞችን ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ወሰነች
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ከቻይናዋ ውሀን ግዛት የሚመጡ መንገደኞች ቦሌ አየር ማረፊያ በሚደርሱበት ጊዜ ከሌሎች መንገደኞች ጋር ሳይቀላቀሉ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡና እና ክትትል እንዲደረግባቸው ወስኗል፡፡
“ከቻይና የሚመጡ መንገደኞችን የጤና ሁኔታ መከታተል እንዲቻል ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቶ” ወደ ስራ ተገብቷል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡
እንደ ሚኒስትሩ መግለጫ ተለይተው ወደ ማቆያ ቦታ የሚገቡት መንገደኞች በማቆያ ቦታ ሆነው የህክምና ክትትል ይደረግላቸዋል፡፡
እስካሁን 29 ጥቆማዎች እንደደረሰው የተናገረው ሚኒስቴሩ ከነዚህ ውስጥ 14 ምልክቱ ስለታየባቸው በበስታው እንዳለባቸውንና እንደሌለባቸው ለመጣራት ሲባል ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
“11 ናሙናዎች ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልከው ስምንቱ ከቫይረሱ ነፃ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ሶስት ናሙናዎች የምርምራው ውጤት እየተጠበቀ” መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
እንደ ዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት እስከአሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር፣ ሰላሳ ሺህ 30,852 ሲሆን፣ 635 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል ፡፡