በቱርክ የርዕደ መሬት አደጋ በፍርስራሽ ተቀብራ የነበረች ሴት ከ3 ቀናት በኋላ በህይወት ተገኘች
እስካሁን በአደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 21ሺ በላይ ሆኗል
በሬክተር ስኬለ 7.8 የተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል
በቱርክ በደረሰው የርዕጀ መሬት አደጋ በፍርስራሽ ውስጥ ተቀብራ የነበረች ሴት በነፍስ አድን ሰራተኞች አማካኝነት በህይወት ከተቀበረችበት ወጥታለች።
በሬክተር ስኬለ 7.8 የተለካው የርዕደ መሬት አደጋ ከፍተኛ ውድመት ከስከትሏል።
የነፍስ አድን ሰራተኞች ሴትዮዋን ከተቀበረችበት የህንጻ ፍርስራሽ ከ104 ሰአታት በኋላ ሲያወጡ በቦታው የነበሩ ተመልካቾች ደስታቸውን ሲገልጹ እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።
የጀርመን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከተደረመሰው የህንጻ ፍርስራሽ ውስጥ የ40 አመቷን ዘይነብ ካህራማንን በስትሬቸር ማውጣት ችለዋል።
"አሁን በተአምር አምናለሁ" ሲሉ የአለም አቀፉ የፍለጋ እና ነፍስ አድን ቡድን መሪ ስቴቨን ባየር ተናግረዋል።
ቡድን መሪው "ሰዎች ሲያለቅሱና ሲተቃቀፉ ታያለህ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የነበረች ሴት መውጣቷ ትለቅ እረፍት ነው፤ ይህ ፍጹም የሆነ ተአምር ነው" ብለዋል።
በደቡባዊ ቱርክ እና በሰሜን ምእራብ ሶሪያ በአስርት አመታ ውስጥ በቀጣናው በተከሰተው ከባድ የርዕደ መሬት አደጋ እስካሁን 21ሺ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።
በአደጋው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤት አልባ ሆነዋል፤ የምግብ እጠረትም አጋጥሟቸዋል ተብሏል።