![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/12/273-160351--6-_167ac8e2752aa4_700x400.jpg)
ሙስና ከተንሰራፋባቸው 10 ሀገራት ስድስቱ በአፍሪካ የሚገኙ ናቸው
ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የ2024 የሀገራት የሙስና ተጋላጭነት ደረጃን ይፋ አድርጓል።
ተቋሙ የ180 ሀገራትን ደረጃ ይፋ ሲያደርግ 47 ሀገራት ደረጃቸው ዝቅ ብሏል፤ 37 ሀገራት ደግሞ አሻሽለዋል።
ባህሬን 17 ደረጃዎችን በማሻሻል ቀዳሚ ስትሆን ኮቲዲቯር፣ ሞልዶቫ እና ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ከ13 እስከ 8 ደረጃዎችን ማሻሻል ችለዋል።
6 ነጥብ 8 ቢሊየን የአለማችን ህዝብ የሙስና ተጋላጭነት አመላካች ነጥባቸው ከ50 በታች በሆኑ ሀገራት ይኖራል ብሏል የተቋሙ ሪፖርት።
ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና ግጭት የሌለባቸው እንደ ዴንማርክ ፣ ፊንላንድ እና ሲንጋፖር ያሉ ሀገራት ከፍተኛውን ነጥብ አግኝተዋል።
ግጭት እና ቀውስ ያለባቸው ሀገራት ደግሞ ከ100 ከሚሰጠው ነጥብ እስከ 8 ነጥብ ይዘው ሙስና የተንሰራፋባቸው ሀገራት ተብለዋል።
የባለፈውን አመት (37 ነጥብ) ያስጠበቀችው ኢትዮጵያ በአንድ ደረጃ ዝቅ ብላ 99ኛ ላይ ተቀምጣለች።
በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ከተቀመጡ 10 ሀገራት መካከል ስድስቱ በአፍሪካ የሚገኙ ናቸው።
በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የሙስና ተጋላጭነት ምዘና ከ100 ነጥብ 8 የተሰጣት ደቡብ ሱዳን የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች። ሶማሊያ ደግሞ በ9 ነጥብ 179ኛ ደረጃ ተቀምጣለች።