የሴት ልጅ ግርዛት የበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት
ምዕራብ አፍሪካዎቹ ጊኒ፣ ማሊ እና ሴራሊዮን በከፍተኛ መጠን የሴት ልጅ ግርዛት ከሚፈጸምባቸው የዓለማችን ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/08/258-171359-whatsapp-image-2025-02-08-at-4.13.43-pm_700x400.jpeg)
ኢትዮጵያ የሴት ልጅ ግርዛት በብዛት ከሚፈጸምባቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት
የሴት ልጅ ግርዛት የበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
የሴት ልጅ ግርዛት ምንም አይነት የጤና ጥቅም ባይኖረውም በበርካታ የዓለማችን ሀገራት በተሳሳተ አመለካከት ምክንያት ይፈጸማል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት መሰረት በጊኒ 94 በመቶ ህጻናት እና ሴቶች ግርዛት የሚፈጸምባቸው ሲሆን በማሊ 88 በመቶ እንዲሁም ሴራሊዮን ደግሞ 83 በመቶ ሴቶች ላይ ይህ ግርዛት ይፈጸምባቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ግርዛትን ለማስቀረት በርካታ የህግ ማሻሻያዎችን እና ፖሊሲዎችን ካወጡ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗ በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡
ከወጡ ፖሊሲዎች መካከል የሴት ልጅ ግርዛት ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መካከል አንዷ መሆኑ፣ በሴቶች ላይ ግርዛት መፈጸም የሰብዓዊ መብት ጥሰት መሆኑ በግልጽ መደንገጉ እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡
የሴት ልጅ ግርዛትን እስከ 2025 ድረስ ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም እቅድ የነበራት ኢትዮጵያ ድርጊቱን ሙሉ ለሙሉ ማስቆም ባይቻልም ግርዛቱ የሚፈጸምባቸው ሴቶች ቁጥር እንዲቀንስ አድርጓል ተብሏል፡፡
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት 2023 ሪፖርት ከሆነ በኢትዮጵያ 65 በመቶ ሴቶች አሁንም ግርዛት ይፈጸምባቸዋል፡፡
ድርጅቱ በመላው ዓለም የሴት ልጅ ግርዛትን በ2030 ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም እቅድ አስቀምጧል፡፡