ኢኮኖሚ
ዲፕሲክ ኤአይን ያገዱ የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
መሰረቱን ቻይና ያደረገው ይህ መተግበሪያ የደህንነት ስጋት ደቅኗል በሚል እገዳ እየተጣለበት ይገኛል

አሜሪካ፣ ጣልያን፣ አውስትራሊያ እና ሌሎችም የዓለማችን ሀገራት በሀገራቸው እንዳይሰራ እገዳ ሲጥሉ በርካታ ሀገራት ደግሞ ጉዳቱን እየመረመሩ ናቸው
ዲፕሲክ ኤአይን ያገዱ የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ከሁለት ሳምንት በፊት መሰረቱን ቻይና ያደረገው ዲፕ ሲክ መተግበሪያ ወይም አፕ በአፕ ስቶር ላይ ከተጫነ በኋላ የበርካታ ተቀወማትን እና ተጠቃሚ ግለሰቦችን ትኩረት ስቧል።
ይህ መተግበሪያ እንደ ጎግሉ ጀሚኒ፣ እንደ ኦፕን አይ ኩባንያው ቻትጅፒቲ እና ሌሎችም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያች ጋር ተመሳሳይ አገልግሎት እንዲሰጥ ተብሎ የተዘጋጀ ነው።
የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያዎችን ቢሊዮን ዶላር ወጪ አድርገው የሰሩ ቢሆንም ይህ የቻይናው ጀማሪ ኩባንያ ግን በትንሽ ወጪ መስራቱ ተገልጻል።
ይህን ተከትሎም አሜሪካንን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ይህን ኤአይ ሞዴል ተጠራጥረው እገዳ በመጣል ላይ ናቸው፡፡
ከአሜሪካ ባለፈ ጣልያን እና አውስትራሊያ እገዳ ሲጥሉ ደቡብ ኮሪያ፣ ቤልጂየም እና ፈረንሳይ ደግሞ በዲፕሲክ ኤአይ ሞዴል ላይ ምርመራ እንዲደረግ አዘዋል፡፡