የየካቲት 12 ሰማእታት ታስበዋል
ከ83 አመታት በፊት በጣሊያን የተገደሉ ሰማእታት ዛሬ ታስበው ውለዋል
ከ83 አመታት በፊት በጣሊያን የተገደሉ ሰማእታት ዛሬ ታስበው ውለዋል
አውሮፓውያን የአፍሪካ ሀገራትን የቅን ግዛት ለማድርግ አይናቸውን ወደ አፍሪካ የማተሩበት የታሪክ ምእራፍ ነበር፡፡ በወቅቱ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት በአውሮፓውያን እጅ ሲወድቁ፣ ኢትዮጵያን ለመውረር ቀይ ባሕርን ያቋረጠችው ጣሊያን ግን ሳይሳካላት ቀርቷል፡፡
በ1888 አድዋ ላይ የጣሊያንን ጦር የገጠመው የኢትዮጵያ ሰራዊት በማሸነፍ ድል ማስመዝገቡ፣ ድሉ የአለምጥቁር ድል ሲባል ጣሊያን የሽንፈት ካባ ተከናንባ የኢትዮጵያን ምድር ለቃ ወጣች፡፡
ነገር ግን በአድዋ ሽንፈት ቂም የያዘችው ጣሊያን ከ35 አመታት በኋላ ተመልሳ በመምጣት ኢትዮጵያን በመውረር ብዙ አትዮጰያዉያንን ገድሏል፡፡
ጊዜው የዓለም መንግስታት ማህበር (League of Nations) የተመሰረተበትነበር፤ ኢትዮጵያ ለዚሁ ማህበር ወረራው ተገቢ አይደለም ብላ አቤት ብትልም አጋርነት ካሳዩ ጥቂት ሀገራት ውጭ ሰሚ አላገኘችም ነበር፡፡
ይሁንና የዓለም መንግስታት ማህበር (league of nations) ከተመሰረተ ከአምስት ዓመታት በኋላ ጣሊያን በድጋሚ ኢትዮጵያ ለመውረር ጦርነት ጀመረች፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ መንግስትና አርበኞች ሃገርን ላለማስደፈር ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል፡፡
ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ የጣሊያንን ድርጊት አዲስ ለተቋቋመው የመንግስታት ማህበር ለማልከት ወደ ውጭ ሃገራት ቢሄዱም ህግና ሉዓላዊነት በወቅቱ ትኩረት ሊሰጣቸው ስላልቻለ ኢትዮጵያውያ የነጻነት ተጋድሏቸውን አጠናክረው ቀጠሉ፡፡
ንጉሰ ነገስቱም በብሪታኒያ እንዲቆዩ ሆነ፡፡ ጣሊያን በአድዋ የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስና ኢትዮጵያ ለመውረር ባደረገው ወረራ የተበሳጩት ሃገር ወዳዶቹ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ከ83 ዓመታት በፊት (የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም) በኢትዮጵያ የፋሺስት ጣሊያን አስተዳደር ተወካይ (ኃላፊ) የነበረውን ማርሻል ሩዶልፎ ግራዚያኒን ለመግደል ሙከራ አደረጉ፡፡ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የወረወሯቸው ቦምቦች ግራዚያኒን ጨምሮ ሌሎች በስፍራው የነበሩ ሹማምንትን አቆሰሉ፡፡
ኢትዮጵያን ለመግዛት ለመውረር 40 አመታትን አቅዶ የመጣው ጣሊያን የባሰ ለግዲያ የሚያነሳሳ ነገር በማግኘቱ ፋሺስቶች የበቀል ሰይፋቸውን በኢትዮጵያውያን ላይ መዘዙ፡፡ በሦስት ቀናት ውስጥም ከ30ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ፋሽስቶች ገደሉ፡፡
የበቀል እርምጃው በአዲስ አበባ ብቻም ሳይሆን በደብረ ሊባስ ገዳምም ደርሶ ቀሳውስትና ምዕመናን እንዲገደሉ መደረጉታሪክ መዝግቦታል፡፡
ከዚያን ግዜ ጀምሮ የካቲት 12 በሃገር ወዳዶች ዘንድ በየዓመቱ ይከበራል፡፡
የየካቲት12 ሰማእታት ድባብ
በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ አሰቃቂና አሳዛኝ ከሆኑት ጭፍጨፋዎች መካከል አንዱ የሆነው የካቲት 12 ጭፍጨፋ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከነበሩ አስከፊ ክስተቶች መካከል ይጠቀሳል፡፡ይህ በርካቶች መስዋዕት የሆኑበት በዓል ታዲያ ባለፉት ዓመታት የተጠበቀውን ያህል አለመከበሩን በርካቶች ያነሳሉ፡፡
የቀድሞው የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት አርበኛ ወርቅነህ ተገኘ በዚህ ሰማዕታትን በሚታሰቡበት ዕለት የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በብዛት መገኘት አንደነበረባቸው ያነሳሉ፡፡
በእርግጥ በዛሬው የመታሰቢያ ክብረ በዓል ቀን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪየ እንዳወቅ አብቴ ቢገኙም አርበኛው ወርቅነህ ግን ሌሎችም መገኘት ነበረባቸው ብለዋል፡፡በፋሽስቶች ወረራ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች የተሰውት ለሃገር ነጻነት ነውና ሁሉም ሊገኙ ይገባ ነበር ብለዋል፡፡
በበርካታ ሃገራዊና ባህላዊ በዓሎች ላይ የሚገኘውና በቅጽል ስሙ ባላገሩ በሚል የሚጠራው ተሸመ አየለ የዘንድሮው በተሻለ ሁኔታ መከበሩን ገልጾ ነገር ግን እንደጠበው አለመከበሩን ነው የገለጸው፡፡
ትውልድን መክሰስና መውቀስ አያስፈልግም የሚለው ባላገሩ ሁሉም ስለሃገሩ ታሪክ ሊያውቅና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብሏል፡፡በመሆኑም በቀጣይ በዓሉን ማሰብና መዘከርና ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ብሏል ተሾመ፡፡
አሁን ላይ ሰማዕታትን የምናስባቸው በጣሊያን ላይ ቂም ለመያዝ ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ምን ያህል ለነጻነታቸው ዋጋ እንድከፍሉ ለማስታወስና ለማስተማር ነው ብሏል፡፡
ታዳጊዎች ምን ይላሉ
የጀርመንት ት/ቤት የ 7ኛ ክፍል ተማሪዎቹ ኃይለማሪያም ምስጋውና ባምላክ ጌታቸው ስለየካቲት 11 በደንብ እንደሚያውቁ ይናገራሉ፡፡ እነርሱ እንደሚሉት ዕለቱ ኢትዮጵያ አንደ ሃገር እንድትቀጥል መስዋዕት የጠከፈለበት ነው ይላሉ፡፡ የዕድሜ እኩዮቻቸውና የሚበልጧቸውም ሰማዕታትን ማሰብ እንዳለባቸው ታዳጊዎቹ ይናገራሉ፡፡ይህን ዕለት ማወቅ የቻሉትም በማንበብና ከቤተሰቦቻቸው በመስማት መሆኑን ያነሳሉ፡፡በቀጣይ ጊዜያት ይህንን የሰማዕታት ዕለት ሁሉም ሊያስበው ይገባል ብለዋል፡፡
የቀድሞዋ ይጎዝላቪያ የአሁኗ ሰረቢያ ለኢትጵያ ነጻነት የበኩሏን አስተዋጽኦ ማድረጓ ዛሬ በነበረው መርሃ ግብር ላይ ተነስቷል፡፤ በኢትጵያ የሰርቪያ አምባሳደር አሌክሳንደር ሪስቲችም በዛሬው የሰማዕታት መታሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተዋል፡፡
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት
ልጅ ዳንኤል ጆቲ በዓሉ በቀጣይ ከዚህ በላይ እንደሚከበር እርግጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ የሰማዕታት ዕለት የሚታሰበው ኢትዮጵያውያን ምን ያህል መስዋዕትነትን እንደከፈሉ ለትውልዱ ለማስተላለፍ ነው ብለዋል፡፡ትውልዱ ይህንን ዕለት ከዚህ በበለጠ ማሰብ አለባቸውም ብለዋል፡፡