አሰልጣኝ ኑኖ እስፒሪቶ የተሰናበቱት በማንችስተር ዩናይትድ በመሸነፋቸው ነው
ቶትንሀም አሰልጣኙን አሰናበተ፡፡
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶትንሀም የወንዶች እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኙን ማሰናበቱን አስታውቋል፡፡
የቀድሞው የዎልቭስ አሰልጣኝ የነበሩት የ47 ዓመቱ ኑኖ እስፒሪቶ ከአራት ወር በፊት ነበር የቶትንሀም ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተቀጠሩት፡፡
ይሁንና በውጤት ማጣት ምክንያት ከአሰልጣኝነታቸው ተሰናብተዋል፡፡
አሰልጣኙ የተሰናበቱት ባሳለፍነው ቅዳሜ በማንችስተር ዩናይትድ 3 ለዜሮ በሆነ ውጤት መሸነፋቸውን ተከትሎ ነው፡፡
“ካፍ በባህርዳር ስታዲየም ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ወቅቱን ያልጠበቀ ነው”- የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት
የአሰልጣኙ ረዳት የሆኑ ኢያን ካትሮ እና ሩይ ባርቦሳን መሰል የቡድኑ አባላት አብረው መሰናበታቸውንም ነው ክለቡ ያስታወቀው፡፡
ቶትንሀም አሰልጣኝ ኑኖ እስፒሪቶን ከቀጠረ በኋላ ካደረጋቸው ሰባት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ውስጥ አምስቱን ተሸንፏል፡፡
ቶትንሀሞች አሁን ላይ በ15 ነጥብ በስምንተኛ ደረጃ ላይ ሲሆኑ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የወቅቱ መሪ ቼልሲ በ10 ነጥቦች ርቀዋል፡፡
የግብፁ ኮኮብ ሞሃመድ ሳላህ “በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ከፍተኛ የሆነ ሳምንታዊ ደሞዝ” ጠየቀ
የቶትንሀም እግር ኳስ ክለብ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ፋቢዮ ፓራሲ እንዳሉት ኑኖ ክለቡን ውጤታማ ለማድረግ ምን ያህል ፍላጎት እንዳላቸው እናውቃለን ነገር ግን ይሄንን ውሳኔ መወሰን ነበረብን ብለዋል፡፡
ክለቡ አሰልጣኙን ካሰናበተ በኋላ ተተኪ አሰልጣኝ በመፈለግ ላይ መሆኑንም አስታወቋል፡፡
የቀድሞው የቼልሲ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ኑኖን ተክተው ቶትንሃምን ሊያሰለጥኑ እንደሚችሉም ተነግሯል፡፡ የብራይተኑ አሰልጣኝ ግርሃም ፖተር እና ፓውሎ ፎንፌካም ለአሰልጣኝነት ከሚፈለጉት መካከል እንደሆኑም ዘገባዎች ያመለከቱት፡፡