ጣልያናዊው አንቶኒዮ ኮንቴ የቶትንሀም አሰልጣኝ ሆነው ተሸሙ
አንቶኒዮ ኮንቴን በሰሜን ለንደኑ እግር ኳስ ክለብ ቶትንሀም እስከ 2023 ድረስ የሚያቆያቸውን ኮንትራት ፈርመዋል
ቶትንሀም ከአራት ወራት በፊት የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ የሾመው ኑኑ እስፒሪቶን ማሰናበቱ ይታወሳል
ጣልያናዊው አንቶኒዮ ኮንቴ የቶትንሀም አሰልጣኝ ሆነው ተሸሙ።
የቀድሞው የቼልሲ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ከአራት ቀናት በፊት ከክለቡ የተሰናበቱን ኑኖ እስፒሪቶን ተክተው የቶትንሃም አሰልጣኝ ሆነዋል።
ኮንቴ በፈረንጆቹ 2017 ከቼልሲ ጋር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ያሸነፉ ሲሆን ከቶትንሀም ጋር እስከ 2023 ድረስ አሰልጣኝ ተደርገው ተሸመዋል፡፡
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶትንሀም የወንዶች እግር ኳስ ክለብ በትናንትናው ዕለት አሰልጣኙን ማሰናበቱን አስታውቋል።
የቀድሞው የዎልቭስ አሰልጣኝ የነበሩት የ47 ዓመቱ ኑኖ እስፒሪቶ ከአራት ወር በፊት ነበር የቶትንሀም ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተቀጠሩት።
ይሁንና በውጤት ማጣት ምክንያት ከአሰልጣኝነታቸው ተሰናብተዋል።
አሰልጣኙ የተሰናበቱት ባሳለፍነው ቅዳሜ በማንችስተር ዩናይትድ 3ለ0 በሆነ ውጤት መሸነፋቸውን ተከትሎ ነው።
የአሰልጣኙ ረዳት የሆኑ ኢያን ካትሮ እና ሩይ ባርቦሳን መሰል የቡድኑ አባላት አብረው መሰናበታቸውንም ነው ክለቡ ያስታወቀው።
ቶትንሀም አሰልጣኝ ኑኖ እስፒሪቶን ከቀጠረ በኋላ ካደረጋቸው ሰባት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ውስጥ አምስቱን ተሸንፏል።
ቶትንሀሞች አሁን ላይ በ15 ነጥብ በስምንተኛ ደረጃ ላይ ሲሆኑ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የወቅቱ መሪ ቼልሲ በ10 ነጥቦች ርቀዋል፡፡