ፕሬዝዳንት ፑቲን አምጾ የነበረው የዋግነር ቡድን ተዋጊዎች በድጋሚ በሩሲያ እንዲያገለግሉ እድል መስጠታቸው ተገልጿል
ፕሬዝዳንት ፑቲን አምጾ የነበረው የዋግነር ቡድን ተዋጊዎች በድጋሚ በሩሲያ እንዲያገለግሉ እድል መስጠታቸው ተገልጿል።
ሮይተረስ የሩሲያውን እለታዊ ጋዜጣ ኮመርሳንት ጠቅሶ እንደዘገበው ፑቲኖ ህዳር መጨረሻ ላይ ከዋግነር መሪ ፕሪጎዥን እና 30 ከሚሆኑ የቡድኑ ተዋጊዎች ጋር በነበራቸው ውይይት በድጋሚ ለሩሲያ የማገልገል እድል ስጥተዋቸው ነበር።
ወይይቱ የተካሄደው በፕሪጎዥን የሚመራው ዋግነር ቡድን በሩሲያ ጦር ላይ የከፈተው አመጽ ከከሸፈ አምስት ቀናት በኋላ ነበር።
የግል ወታደራዊ ቡድን ማደራጀት እና ህጋዊ አሰራር ማበጀት የሩሲያ መንግስት እና ፖርላመንት ኃላፊነት ነው ሲሉም ተደምጠዋል ፑቲን።
ፑቲን ከፕሪጎዥን እና 35 ከሚሆኑ የቡድኑ ወታደሮች ጋር በነበራቸው ወይይት በአሁኑ አዛዣቸው ስር 16 ወራት መቆየትን ጨምሮ በርካታ የወደፊት እጣፋንታ አማራጮችንም አቅርበው ነበር ተብሏል።
"ሁሉም በአንድ ቦታ ሆነው አገልግሎታቸውን መስጠት ይችላሉ፤ ምንም የሚቀየር ነገር የለም" ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ ጨምሮ ዘግቧል።
የዋግነር ቡድን አንስቶት የነበረውን አመጽ የተወው በቤላሩስ አደራዳሪነት ነበር
በድርድሩ መሰረት የዋግነር መሪ ፕሪጎዥን ወደ ቤላሩስ እንዲዛወር እና በሩሲያ የተመሰረተበት ክስ መነሳቱ ይታወሳል።