![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/14/258-075341--_167aebe4581dd0_700x400.png)
በምዕራቡ ዓለም የሚከበረው የፍቅረኛሞች ቀን በፈረንጆቹ የካቲት 14 ይከበራል
ቫላንታይን ቀን እንዳይከበር ያገዱ የዓለማችን ሀገራት
በሮማዊያን አገዛዝ ዘመን ይኖር እንደነበር የሚገለጸው ቅዱስ ቫላንታይን የክርስትና ሀይማኖት መምህር እንደሆነ ይገለጻል።
በዚያ አገዛዝ ዘመን ወንዶች ለጦርነት እና ሌሎች ወታደራዊ ዘመቻዎች መፈለጋቸውን ተከትሎ ፍቅረኛ እንዳይዙ እና እንዳያገቡ ይከለከሉ እንደነበር በጉዳዩ ዙሪያ የተጻፉ ታሪኮች ያስረዳሉ።
በወቅቱ መምህር የነበሩት ቅዱስ ቫላንታይን ግን በድብቅ ፍቅረኞችን ይባርኩ እና ያጋቡም ነበር ተብሏል።
የቄስ ቫላንታይን ድርጊት በንጉሶች ከታወቀ በኋላ ግን በፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር የካቲት 14 ቀን በስቅላት እንደተቀጡ ይገለጻል።
ይህን ተከትሎም ቄስ ቫላንታይን ለፍቅር ሲሉ በከፈሉት መስዋዕትነት ቅዱስ ተብለው መጠራት ሲጀምሩ ዕለቱም የፍቅረኛሞች ቀን ተብሎ እየተከበረ ይገኛል።
በምዕራቡ ዕለም በደማቅ የሚከበረው ይህ በዓል በተወሰኑ ሀገራት ደግሞ በዓሉን ማክበር ይከለክላሉ።
ማሌዥያ፣ ኢራን፣ የሩሲያዋ ቤሎጎሮድ ክልል፣ ሳውዲ አረቢያ እና ኢንዶኔዥያ ደግሞ በዓሉን ከከለከሉ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።