ዜጎቻቸው ልጆችን እንዲወልዱ የሚያበረታቱ የዓለማችን ሀገራት
ሀገራት ለዜጎቻቸው ግብር ከመቀነስ ጀምሮ የተለያዩ ማበረታቻዎን እየሰጡ ይገኛሉ

ሲንጋፖር፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጣልያን እና ሀንጋሪ ዜጎቻቸው ብዙ ልጆችን እንዲወልዱ ከሚያበረታቱ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
ዜጎቻቸው ልጆችን እንዲወልዱ የሚያበረታቱ የዓለማችን ሀገራት
ከ50 ዓመት በፊት ከስምንት ሀገራት በስተቀር በቀሪዎቹ የዓለማችን ሀገራት አንዲት ሴት ቢያስ ሁለት ሴት ልጆችን ትወልድ ነበር፡፡
አሁን ላይ አንዲት ሴት በህይወት ዘመኗ ከሁለት በታች ልጆችን የምትወልድባቸው ሀገራት ብዛት 98 ደርሷል፡፡
በርካታ የዓለማችን ሀገራት የኢኮኖሚ ግስጋሴያቸውን ለማስቀጠል ቢፈልጉም በአንጻሩ የሚወለዱ ህጻነት ቁጥር ግን እየቀነሰ ይገኛል፡፡
ይህን ተከትሎም በርካታ ሀገራት ዜጎቻቸው ልጆችን እንዲወልዱ የገንዘብ ማበረታቻዎችን፣ አገልግሎቶች በነጻ እና በቅናሽ ማቅረብ፣ ስጦታዎችን መስጠት እና ሌሎች ማበረታቻዎችን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
ለአብነትም ሀንጋሪ ሶስት እና ከዚያ በላይ ልጆችን ለሚወልዱ ዜጎቿ ግብር እንዳይከፍሉ ስትፈቅድ ጃፓን፣ ቻይና እና ሲንጋፖር ደግሞ የሰርግ ወጪዎችን መሸፈን፣ የገንዘብ ስጦታዎች እና አገልግሎቶችን በነጻ አልያም በቅናሽ እናቀርባለን ብለዋል፡፡
ጣልያን፣ ካናዳ እና ጀርመን ደግሞ የመኖሪያ ቤቶች ወጪን መጋራት፣ ግብር መቀነስ እና ሌሎች ባለትዳሮች ተረጋግተው እንዲኖሩ እና ልጆችን እንዲወልዱ የሚያደርጉ አሰራሮችን ዘርግተዋል፡፡