ኢለን መስክ ለ14ኛ ጊዜ የልጅ አባት መሆኑ ተገለጸ
የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆነው ኢለን መስክ ሰዎች ብዙ ልጆችን እንዲወልዱ በማበረታታት ይታወቃል

ባለጸጋው ከአራት ሴቶች የተወለዱ የ14 ልጆች አባት ነው ተብሏል
ኢለን መስክ ለ14ኛ ጊዜ የልጅ አባት መሆኑ ተገለጸ፡፡
የ352 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት ባለቤት የሆነው ኢለን መስክ ለ14ኛ ጊዜ የልጅ አባት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ቴስላ፣ አክስ፣ ኒውራሊንክ እና ሌሎች በርካታ ኩባንያዎችን የመሰረተው እና ባለቤት የሆነው ኢለን መስክ በቅርቡ ወንድ ልጅ አባት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በኢለን መስክ ንብረቶች ስር አንዱ የሆነው ኒውራሊንክ ኩባንያን በሀላፊነት እየመራች ያለችው ሺቮን ዚሊስ በኤክስ አካውንቷ ላይ ከኢለን መስክ የወለደችውን ወንድ ልጅ ልደት እንደምታከብር ገልጻለች፡፡
ኢለን መስክ ከዚሊስ ጋር አንድ መንታን ጨምሮ ሶስት ልጆችን የወለዱ ሲሆን እንደምታፈቅረውም በጽሁፏ ላይ ጠቅሳለች፡፡
ይሁንና ልደቱ የሚከበርለት ልጅ መቼ እንደተወለደ ያልተገለጸ ሲሆን አባት ነው የተባለው ኢለን መስክ የልጁ እናት ፖሰት ላይ የመውደድ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ሰዎች ልጅ እንዲወልዱ የሚያበረታታው ኢለን መስክ ከአራት የተለያዩ ሰዎች 14 ልጆች እንዳሉት ተገልጿል፡፡
ባለጸጋው አሁን ላይ አዲሱን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳድርን እያገዘ የሚገኝ ሲሆን በተለይም የተቋማት ውጤታማነት እና በጀት ቅነሳ ስራዎች ላይ በስፋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
ከልጆቹ እናት ጋር መልካም ግንኙነት እንደሌለው የሚገለጸው ኢለን መስክ በተለይም ከሶስት ልጆችን ከወለደለችለት ካናዳዊቷ ሙዚቀኛ ግሪም ጋር አለመግባባቶች ተከስተዋል፡፡