ኢኮኖሚ
የሚሊየነሮች ብዛት በፍጥነት የጨመረባቸው 10 ሀገራት
በቬትናም፣ ቻይና እና ሞሪሺየስ ባለፉት 10 አመታት በርካታ አዳዲስ ባለሃብቶች የሚሊየነሮችን ጎራ ተቀላቅለዋል
በናይጀሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ጃፓን በአንጻሩ የሚሊየነሮች ቁጥር ዝቅ ብሏል
በአለማችን የዶላር ሚሊየነሮች ቁጥር ከ59 ሚሊየን መሻገሩን ኪፕሊንገር የተሰኘው የአሜሪካ መጽሄት ገልጿል።
ከዚህ ውስጥ ከ24 ሚሊየን በላዩ (ከጠቅላላው 39 በመቶ) በአሜሪካ የሚገኙ ናቸው።
ቻይና በ6 ነጥብ 2 ሚሊየን እንዲሁም ፈረንሳይ በ2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሚሊየነሮች አሜሪካን ይከተላሉ።
እንደ ናይጀሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ብሪታንያ፣ ጃፓን፣ ሩሲያ እና ብራዚል ያሉ ሀገራት ደግሞ የሚሊየነሮቻቸው ቁጥር እየቀነሰባቸው ነው።
በተለያዩ አለማቀፍ ጫናዎች ከሚሊየነርነት የወረዱ በርካታ ባለጠጎች የመኖራቸውን ያህል በአንዳንድ ሀገራት በርካታ ሰዎች በፍጥነት የሚሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ ይገባሉ።
የግሎባል ዌልዝ ሪፖርት እንደሚያመላክተው በ2027 በአለማቀፍ ደረጃ 86 ሚሊየን ሰዎች የዶላር ሚሊየነር ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ባለፉት 10 አመታት የሚሊየነሮቻቸው ቁጥር በፍጥነት የጨመረባቸውን ሀገራት ዝርዝር ይመልከቱ፦