ኢኮኖሚ
ሚሊየነሮች የሚፈልሱባቸው 10 የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ቻይና፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሕንድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሚሊየነሮቻቸውን እያጡ ነው ተብሏል
አረብ ኢምሬት፣ አሜሪካ እና ሲንጋፖር ደግሞ ሚሊየነሮችን በመሳብ ቀዳሚ ሀገራት ሆነዋል
ሚሊየነሮች የሚፈልሱባቸው 10 የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ባለጸጋዎች ለስራዎቻቸው እና ህይወታቸው ምቾት ፍለጋ ከሀገር ሀገር በመዘዋወር ይታወቃሉ፡፡
በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሚሊየነሮች አንድን ሀገር ለቀው ወደ ሌላ ሀገር በመሰደድ ለይ መሆናቸውን በዚህ ዙሪያ ጥናት በማጥናት የሚታወቀው ሀንሌይ ኤንድ ፓርትነርስ የተሰኘው ተቋም ይፋ አድርጓል፡፡
እንደዚህ ተቋም ሪፖርት ከሆነ ቻይና በተያዘው ዓመት ብቻ 15 ሺህ 200 ሚሊየነሮቿ ወደ ሌሎች ሀገራት ሲሰደዱ፣ ብሪታንያ ደግሞ 9 ሺህ 500 ሚሊየነሮች እንዲሁም ሕንድ 4ሺህ 300 ሚሊየነሮች ተሰደዋል፡፡
የቻይና ሚሊየነሮች ሲንጋፖር፣ ካናዳ እና አሜሪካንን ዋነኛ መዳረሻቸው አድርገዋል ተብሏል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ግን የተባበሩት አረብ ኢምሬት፣ አሜሪካ እና ሲንጋፖር የዓለማችን ዋነኛ የሚሊየነሮች የስበት ማዕከል ሆነዋል፡፡