ትዳርን መፍታት ከባድ የሆነባቸው የዓለማችን ሀገራት
ሕንድ ፣ ሩሲያ እና ችሊ በትዳር ላይ ባጋጠመ ስህተት ምክንያት ትዳር ማፍረስ ክልክል ነው

በፊሊፒንስ ጥንዶች ከተጋቡ በኋላ ትዳርን መፍታት የማይቻል ሲሆን የግድ ፍቺ ከፈጸሙ ግን ሁለቱም ዳግም ማግባት አይችሉም
ትዳርን መፍታት ከባድ የሆነባቸው የዓለማችን ሀገራት
በጥንዶች ፈቃደኝነት የሚፈጸመው ጋብቻ ወይም ትዳር በሁሉም ሀይማኖቶች የሚበረታታ ተግባር ነው።
በርካታ የዓለማችን ሀገራት ለቤተሰብ መመስረት ዋነኛው ነው የሚባለው ትዳር እንዲደረጅ የተለያዩ ድጋፎችን ያደርጋሉ።
ከነዚህ መካከልም ግብር መቀነስ፣ ስጦታዎችን ማበርከት፣ ወጪዎችን መጋራት እና ሌሎች የስነ ልቦና ድጋፎችንም ያደርጋሉ።
ይህ በዚህ እንዳለ ግን የተመሰረቱ ትዳሮች እንዳፕፈርሱ በሚል ጥብቅ ህግ የሚከተሉ ሀገራትም አሉ።
ለአብነትም እስያዊቷ ፓኪስታን ትዳርን ለመፍታት ብዙ ውጣ ውረዶችን የሚጠይቁ ህጎች አሏት።
ለአብነትም አንዴ የተፋቱ ባልና ሚስቶች ራሳቸው አልያም ከሌላ የፍቅር አጋር ጋር ጋብቻ እንዳይመሰርቱ ትከለክላለች።
ቺሊ፣ ሩሲያ፣ ሕንድም እና ሉግዘምበርግም ትዳር በቀላሉ እንዳይፈርስ በሚል ባል ወይም ሚስት ጥፋት አጥፍተዋል ብለው ፍቺ እንዲፈጸም በፍርድ ቤት መጠየቅ እንደማይችሉ ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው ገልጿል።