በንጽህና ጉድለት ምክንያት የፈረሰው ትዳር
ባልየው ገላዬን በወር አንዴ ብቻ ነው የምታጠበው ማለቱን ተከትሎ የጥንዶቹ ትዳር ፈርሷል
ሚስትየው ባሏ አልታጠብም በማለቱ ከተጋቡ ከ40 ቀናት በኋላ ተፋተዋል
በንጽህና ጉድለት ምክንያት የፈረሰው ትዳር
በሕንዷ ኡታር ፕራዲሽ አግራ በተሰኘችው ከተማ የሚኖሩት ባልና ሚስት ከ40 ቀናት በፊት ነበር ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የተጋቡት፡፡
ይሁንና ባልየው ገላዬን በወር አንዴ ብቻ ነው የምታጠበው በማለቱ ምክንያት ከሚስቱ ጋር ግጭት ውስጥ ይገባሉ፡፡
ልብሶቹን ሳይቀር አቆሽሾ መልበስ የሚፈልገው ይህ ባልም የሚስቱን ፍላጎት እና ስሜት ማክበር ባለመቻሉ ትዳሩ ፈርሷል፡፡
በሕንድ ከዕምነት ጋር በተያያዘ ሰውነትን እና ልብሶችን ቶሎ ቶሎ አለመታጠብ የሚዘወተር ሲሆን ይህ ባልም ገላውን የማይታጠበው ከዚሁ ጋር በተገናኘ እንደሆነ ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
የባልየው ቤተሰቦች ወደ ሚስት ቤተሰቦች በመሄድ ጥንዶቹን ሊግባቡ እና ሊያስታርቋቸው ቢሞክሩም ቢሞክሩም ባለትዳሮቹ ወደ ቀድሞ ትዳራቸው ሊመለሱ እንዳልቻሉም ተገልጿል፡፡
ኒውዮርክ በትዳር አጋራቸው ላይ የማገጡ ሰዎችን የሚቀጣውን ህግ ልታነሳ ነው
ከዚህ በፊት በታይዋን የሚኖሩ ባልና ሚስት ከዚሁ ከንጽህና ጋር በተያያዘ ለፍቺ የተዳረጉ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ሚስትየው ሻወር የምትወስደው በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በመሆኑ ነበር፡፡
ይህች እንስት የጥርሷን እና ጸጉሯን ንጽህና በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ እንደምትጠብቅ የተገለጸ ሲሆን የባህሪ ለውጡ ከሰርጋቸው በኋላ መሆኑን ባልየው በወቅቱ ለፍርድ ቤት ተናግሯል፡፡