በርካታ ዜጎቻቸው ኢንተርኔት የማያገኙባቸው 10 ሀገራት
ቻይና በአለማችን ከፍተኛውን የኢንተርኔት ተጠቃሚ ብታስመዘግብም፥ ኢንተርኔት የማያገኙ ዜጎቿ ቁጥር ከአለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል
በመላው አለም 5 ቢሊየን ሰዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ያገኛሉ
የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 5 ቢሊየን የደረሰ ሲሆን፥ ምስራቅ እስያ 1 ነጥብ 24 ቢሊየን ተጠቃሚ በማስመዘገብ ቀዳሚ ነው።
የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የኢንተርኔት ተደራሽነት ግን በጣም ዝቅተኛ ነው ይላል የስታቲስታ ጥናት።
እስከ ጥር 2023 ባለው መረጃ ለበርካታ ዜጎቿ የኢንተርኔት አገልግሎት በማቅረብ ቻይናን የሚደርስባት የለም።
በህንድ የአለማችን ባለብዙ ህዝብ ደረጃዋን ልትነጠቅ የተቃረበችው ቻይና፥ ከ1 ቢሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎቿ ኢንተርኔት ተደራሽ አድርጋለች።
ይህም ከአሜሪካ በሶስት እጥፍ የሚበልጥ ቢሆንም፥ ከህዝብ ብዛቷ አንጻር አሁንም ኢንተርኔት የማያገኙ ዜጎቿ ቁጥር ከአለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።
10ሩ በርካታ ዜጎቻቸው ኢንተርኔት የማያገኙባቸው ናቸው ተብለው በስታቲስታ የተዘረዘሩትን ሀገራት ይመልከቱ፦