10 ስደተኞችን በመቀበል ቀዳሚ ሀገራት
ኢራን እና ቱርክ ከ3 ሚሊየን በላይ ስደተኞችን ተቀብለው በማስተናገድ ቀዳሚዎቹ ናቸው
ሶሪያ፣ አፍጋኒስታን እና ዩክሬን ደግሞ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎቻቸው ለስደት የተዳረጉባቸው ሀገራት ናቸው
ጦርነት፣ ግጭት፣ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ግድያን ሸሽተው ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ባለፈው አመት 110ሚሊየን ደርሷል።
ከዚህ ውስጥ ከ62 ሚሊየን በላዩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሲሆኑ፥ ከ36 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ደግሞ ድንበር አቋርጠው በሌሎች ሀገራት ስደተኛ ሆነዋል ይላል የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ።
አሃዙ ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል የሚጠቅሰው ኤጀንሲው አብዛኞቹን ስደተኞች የሚያስተናግዱት ግጭት ወይም ጦርነት የተከሰተባቸው ሀገራት አጎራባቾች መሆናቸውን ያክላል።
ኢራን በርካታ ስደተኞችን በመቀበል ቀዳሚዋ ሀገር ናት። በኢራን የሚኖሩ ስደተኞች ቁጥር በ2021 ከነበረበት 798,343 በ2023 አጋማሽ ወደ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን አሻቅቧል። አብዛኞቹ ስደተኞችም አፍጋኒስታናውያን መሆናቸውን የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ ይገልጻል።
ሁለተኛዋ ስደተኛ ተቀባይ ሀገር በሆነችው ቱርክም ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ስደተኞች ሶሪያውያን ናቸው።
የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያሳየው ሶሪያ፣ አፍጋኒስታን፣ ዩክሬንና ደቡብ ሱዳን ዜጎቻቸው ለስደት የተዳረጉባቸው ቀዳሚዎቹ ሀገራት ናቸው።
በሶሪያ 6 ነጥብ 5 ሚሊየን፣ በአፍጋኒስታን 6 ነጥብ 1 ሚሊየን፣ በዩክሬን 5 ነጥብ 9 ሚሊየን እንዲሁም በደቡብ ሱዳን 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች ጦርነትን ሽሽት ወደተለያዩ ሀገራት ለመሰደድ ተገደዋል።
እስከ2023 አጋማሽ በርካታ ስደተኞችን ተቀብለው በማስተናገድ ላይ የሚገኙ ሀገራትን ይመልከቱ፦