ከጥቅምት 7 ወዲህ እስራኤል በየትኞቹ ሀገራት ላይ ጥቃት ፈጽማለች?
እስራኤል 10 ወራትን ባስቆጠረው ጦርነት የጋዛን ጨምሮ ከ17 ሺህ በላይ ጥቃቶችን ፈጽለማች
በእስራኤል ጥቃቶች እስካሁን ከ41 ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል
የእስራኤል እና ሃማስ የጋዛ ጦርነት 10 ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ እስራኤል ከሰሞኑ በሊባኖስ እና በኢራን የፈጸመቻቸው ጥቃቶች ቀጠናዊ ስጋትን ከፍ አድርገውታል።
እስራኤል ባሳለፍነው ሳምንት በሰዓታት ልዩነት በሊባኖስ ውስጥ የሄዝቦላ ወታደራዊ መሪ ፉአድ ችኩርን እንዲሁም በኢራን ውስጥ የሃመስ መሪ ኢስማኤል ሃኒየህ መግደሏ ይታወሳል።
ከሃማስ ጋር ጦርነት ከጀመረች ወዲህ በተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ላይ ጥቃት የሰነዘረችው እስራኤል 10 ወራትን ባስቆጠረው ጦርነት የጋዛን ጨምሮ በተለያዩ የመካለኛው ምስራቅ ሀገራ ከ17 ሺህ በላይ ጥቃቶችን ፈጽለማች።
እስራኤል በየትኞቹ ሀገራት ላይ ጥቃት ፈጽማለች?
የጥምቅምት 7ቱን የሃማስ ጥቃትን ተከትሎ እስራኤል ፊልስጤምን ጨምሮ በ5 የመካከለኛው መስራቅ ሀገራት ላይ ከ17 ሺህ በላይ ጥቃቶችን ሰንዝራለች።
የእስራኤል ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሀገራትም ፍሊስጤም፣ ሊባኖስ፣ ሶሪያ፣ የመን እና ኢራን መሆናቸውን የኮንፍሊክት ሎኬሽን ኤንድ ኢቨንት ዳታ ፕሮጅክት መረጃ ያመለክታል።
እስራኤል በሀገራቱ ላይ ምን ያክል ጥቃት ሰንዝራለች፤ ያስከተለው ጉዳትስ?
እስራኤል የጥቅምት 7ቱን የሃማስ ድነገተኛ ጥቃት ተከትሎ ከፍተኛ ድብደባ የተፈጸመችባት የሃማስ መቀመጫ የሆነችው ፊልስጤም ቀዳሚዋ ነች።
ባለፉት 10 ወራት እስራኤል በፍሊስጤም በተለይም ላይ 10 ሺህ 389 ጥቃችን የሰነዘረች ሲሆን፤ በዚህም 40 ሺህ 39 ሰዎች ገድላለች።
ሊባኖስ በርካታ ድብደባን ያስተናገደች ሁለተኛዋ ሀገር ሲሆን፤ ባለፉት 10 ወራት እስራኤል በሊባኖስ ላይ 6 ሺህ 544 ድብደባዎችን ሰንዝራ፤ 590 ሰዎችን ደግላለች።
ሶሪያም 144 ድበደባ የተፈጸመባት ሲሆን፤ 260 ሰዎች በእስራኤል ድብደባ ተገድለዋል።
2 ጊዜ ድብደባ የተፈጸመባት የመን 6 ሰዎች ሲገደሉ፤ በኢራን ላይም 2 ጊዜ በእስራኤል ድብደባ ተፈጽሞ 1 ሰዉ ሞቷል።