እስራኤል ባሳለፍነወ ሳምንት ከፍተኛ የሄዝቦላ አመራር መግደሏ ይታወሳል
የሊባኖሱ ሄዝቦላህ በትናንትናው እለት ወደ እስራኤል በርካታ ሮኬቶቸን መተኮሱን አስታውቋል።
በኢራን እንደሚደገፍ የሚነገርለት እና በሊባኖስ ውስጥ የሚነቀሳቀሰው ሄዝቦላህ “ካይቱሻ” የተባሉ ሮኬቶች ወደ እስራኤል መተኮሱ ነው የተገለጸው።
በቅርብ ከተደረጉ የሮኬት ጥቃቶች ውስጥ ግዙፉ ነው የተባለው የትናንትናው የሮኬት ጥቃት ለፊልስጤም ህዝቦች ድጋፍ የተደረገ መሆኑን ቡድኑ አስውቋል።
በተጨማሪም ቡድኑ በትናንትናው እለት በሰሜናዊ እስራኤል በምትገኘው ቤይት ሂለል ላይ የተፈጸመው ጥቃት እስራኤል በሊባኖስ ከፋር ኬላና ዴር ሳሪን ለፈጸመችው ጥቃት አጸፋ መሆኑንም ገልጿል።
እስራኤል ባሳለፈነው ሳመንት በሰዓታት ልዩነት ውስጥ የሄዝቦላ እና የሀማስ ከፍተኛ አመራሮች መግደሏን ተከትሎ ሊኖር የሚችለው የአጸፋ ምላሽ ቀጠናዊ ግጭትን ሊቀሰቀስ እንደሚችል ተሰግቷል።
ኢራን በእስራኤል ላይ ከፍተኛ የበቀል እርምጃ እንደምትወስድም ዝታለች፡፡
የተባሩት መንግስታ ጸጥታው ምክር ቤት የአመራሮቹን ግድያ ተከትሎ ሂዝቦላ እና ኢራን በእስራኤል ላይ የአጸፋ ጥቃት የሚሰነዝሩ ከሆነ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡