የብሪታኒያ ንጉስ ቻርልስ በዓለማችን ላይ ላሉ 15 ሉዓላዊ ሀገራት ርእሰ ብሄር ናቸው
የንጉሥ ቻርለስ ሦሰተኛ የንግሥና ሥነ ሥርዓት በዛሬው እለት በታላቅ ዝግጅት ለንደን ውስጥ ተካሂዷል።
ይህንን ተከትሎ የንግስት ኤልሳቤጥ የመጀመሪያ ልጅ ንጉስ ቻርልስ የንግስና አክሊልን ዛሬ ደፍተዋል።
በዚህም ንጉስ ቻርልስ ንግስት ኤላሳቤጥ በግንስና ዘመናቸው ከሀገራቸው በተጨማሪ ርእሰ ብሄር በነበሩባቸው ሀገራት ላይም ርእሰ ብሄር በመሆን ይመራሉ።
ሀገራቱ ከዚህ ቀደም የእንግሊዝ ቀኝ ግዛት የነበሩ ሲሆን፤ ከቀኝ ግዛት ከተላቀቁ በኋላም ግን ሀገራቱ የብሪታኒያ ንጉሳውያንን በሀገራቸው ርእሰ ብሄር አድረገው ሾመዋል።
የብሪታኒያ ንጉስ ርእሰ ብሄር የሆኑባቸው 15 ሀገራት የትኞቹ ናቸው..ʔ
1. ካናዳ
2. ጃማይካ
3. አውስትራሊያ
4. ኒውዚላንድ
5. በሃማስ
6. ፓፑዋ ኒው ጊኒ
7. ሰለሞን ደሴቶች
8. በሊዝ
9. ሴንት ኪትስ እና ኔቪስ
10. ሴንት ሉሲያ እና ገራኒድስ
11. ቱቫሉ
12. አንቲጉዋ እና ባበርቡዳ
13. ግሬናዳ
14. ሰለሞን ደሴቶች እንዲሁም
15. ብሪታኒያ ናቸው
ነቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ሀገራት ውስጥ የቢሪታኒያ ንጉሳውያንን ከሀገራቸው ርእሰ ብሄርነት የማንሳት እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል።
ጃማይካ የብሪታንያን ንጉስ በመተው የራሷን መሪ መምረጥ እንደምትፈልግ በቅርቡ ማስታወቋ ይታወሳል።
የብሪታኒያ ቅኝ ግዛት የነበረችው አንቲጓና ባርቡዳ ደሴት የብሪታኒያ ንጉሳውያንን ከርዕሰ በሄርነት በማንሳት ሪፐብሊክ ለመሆን የሚያስችላትን ህዝበ ውሳኔ ልታካሂድ መሆኑን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ጋስቶን ብራዎን አስታውቀዋል።
አንቲጓና ባርቡዳ በፈረንጆቹ 1981 ከቅኝ ግዛት ነጻ ብትወጣም፤ የበሪታኒያ ንግስት ግን የሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር ነበሩ።
ደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ባርባዶስ ባሳለፍነው ዓመት ህዳር ወር ላይ የብሪታኒያ ንጉሰውያንን ከርዕሰ ብሄርነት በማንሳት ሪፐብሊክነቷን ማወጇ ይታወሳል።