ጃማይካ ከብሪታንያ ቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣች 61 ዓመት ቢሆናትም አሁንም የብሪታንያ ንጉስን እንደ መሪ ትቀበላለች
ጃማይካ የብሪታንያን ንጉስ በመተው የራሷን መሪ መምረጥ እንደምትፈልግ አስታወቀች።
ብሪታንያ የዓለም ልዕለ ሀያል በሆነችበት ወቅት ከ600 ሺህ በላይ አፍሪካዊያንን ለኢንዱስትሪዎቿ ጥሬ እቃ ለማሟላት በሚል ወደ ጃማይካ ማምጣቷን የሀገሪቱ ታሪክ ያስረዳል።
የባሪያ ንግድ በ1834 ከታገደበት ጊዜ ጀምሮም በባሪያ ንግድ ወደ ጃማይካ የሆኑ ጥቁር ዜጎች በዛው ኖረው ሀገር መስርተዋል ተብሏል።
ብዙ የባሪያ ንግድ እና የቅኝ ግዛት ጉዳቶች ከደረሰባቸው ሀገራት መካከል ዋነኛዋ የሆነችው ጃማይካ ከብሪታንያ እስካሁን ካሳ እና ይፋዊ ይቅርታን እንደምትፈልግ አስታውቃለች።
14 ሀገራትን የሚመሩት የብሪታንያ ንጉስ ቻርልስ የነገሱበት አንደኛ በዓለ ሲመት በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚከበር ተገልጿል።
በንጉስ ቻርልስ ከሚመሩት ሀገር አንዷ የሆነችው ጃማይካ ከብሪታንያ ንጉስ ይልቅ የራሷን መሪ መምረጥ እንደምትፈልግ ሮይተርስ ዘግቧል።
ጃማይካ ከብሪታንያ ቅኝ ግዛት በፈረንጆቹ 1962 ጀምሮ ነጻ የወጣች ሀገር ተብላ አሁን ደግሞ በብሪታንያ ንጉስ መመራቷ ስህተት ነው ተብሏል።
ባርባዶስ ከዚህ በፊት ብሪታንያ ንጉስን ባለመቀበል የራሷን ሪፐብሊክ መሪ መምረጧ ይታወሳል።
አንቲጉዋ፣ ባርቡዳ፣ ቤሊዝ እና በሀማስ ከብሪታንያ ንጉሳዊ አመራርነት የመውጣት እንቅስቃሴ ከጀመሩ ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ።
ትሪንዳድ እና ቶቤጎ እንዲሁም ዶምኒካ ደግሞ ከዓመታት በፊት ከብሪታንያ ንጉሳዊ አገዛዝ ነጻ የሆነ የራሳቸውን መሪ መምረጣቸው ይታወሳል።
ጃማይካም የነ ባርባዶስን መንገድ ለመከተል መንገድ የጀመረች ሲሆን ይህን ለማድረግ ግን ከሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ ማጽደቅ ይኖርበታል ተብሏል።
ንጉስ ቻርልስ በአሁኑ ወቅት የ14 ሀገራት ንጉሳዊ መሪ ሲሆኑ ካናዳ እና አውስትራሊያ ዋነኞቹ ናቸው።