የአሜሪካው ፎርድ ኩባንያ የኤሌክትሪክ መኪና የማምረት እቅዱን አራዘመ
ኩባንያው ከ2025 ጀምሮ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከባድ መኪኖችን የማምረት እቅድ ነበረው
የኤሌክትሪክ መኪና ፍላጎት አሁንም ዝቅተኛ መሆኑ ለኩባንያው እቅድ መራዘም ምክንያት ነው ተብሏል
የአሜሪካው ፎርድ ኩባንያ የኤሌክትሪክ መኪና የማምረት እቅዱን አራዘመ፡፡
ዋና መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ፎርድ ኩባንያ ከፈረንጆቹ 2025 ጀምሮ ከባድ የኤሌክትሪክ መኪኖችን የማምረት ውጥን አስቀምጦ ነበር፡፡
በዓለም ላይ ያለው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የከባድ ተሽከርካሪዎች ፍላጎት ዝቅተኛ በመሆኑ ኩባንያው እቅዱን በሁለት ዓመት ማራዘሙን አስታውቋል፡፡
ከ2027 ጀምሮም በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከባድ ተሽከርካሪዎችን ማምረት እጀምራለሁ የሚለው ፎርድ ኩባንያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ማምረቴን እቀጥላለሁም ብሏል፡፡
ድርጅቱ የኤሌክትሪክ ከባድ ተሽከርካሪዎችን ማምረት እጀምራለሁ በሚል 2 ሺህ 700 ሰራተኞቹን ለማሰናበት በዝግጅት ላይ የነበረ ሲሆን ምርቱ በመዘግየቱ ምክንያት ሰራተኞቹ እንዲቀጥሉ ስለመስማማቱም በዘገባው ላይ ተገልጿል፡፡
የቻይናው የስልክ ቀፎ አምራቹ ሺዮሚ የተሰኘው ኩባንያ የኤሌክትሪክ መኪና ማምረት ጀመረ
ሌላኛው የአሜሪካ ቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የማምረት እቅዱን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ይታወሳል፡፡
የቻይናው ዢዮሚ የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪውን አምርቶ ለገበያ አቅርቧል፡፡
ኩባንያው ሱ7 የተሰኘ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ በ69 ሺህ ዶላር ለዓለም ገበያ ያቀረበ ሲሆን የቻይና ኩባንያዎች የዓለምን ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ገበያን እየተቆጣጠሩ ይገኛሉ፡፡