ፌስቡክ በአንደኛ ደረጃ በጣም ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ ማህበራዊ የትስስር ነው
በርካታ ተጠቃሚዎች ካሉት የማህበራዊ ትስስር ገጾች ውስጥ ፌስቡክ አነዱ እና አንደኛው ሲሆን፤ በዓለም ዙሪያ በቢሊየን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች እንዳት ይታወቃል።
ከእነዚህም ውስጥ በህንድ ብቻ ወደ 315 ሚሊዮን የሚጠጉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የተባለ ሲሆን፤ ይህም ሀገሪቷን በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ብዛት ቀዳሚ አድርጓታል።
በሌላ አገላለጽ የህንድ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በዓለም የህዝብ ቁጥር ቢቀመጥ በብዛቱ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣሉ።
ከህንድ በመቀጠል እያንዳንዳቸው ከ100 ሚሊዮን በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ያሏቸው በርካታ ሀገራት አሉ።
አሜሪካ 175 ሚሊዮን፣ ኢንዶኔዥያ 119 ሚሊዮን እና ብራዚል 109 ሚሊዮን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች አሏቸው።
እስከ ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ድረስ በኢትዮጵያ በጣም ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ የሆነው ፌስቡክ፤ ወደ 7 ሚሊዮን የሚጠጉ ተጠቃሚዎች አሉት።
ፌስቡክ ሜሴንጀር ደግሞ ወደ ስድስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ተጠቃሚዎች አሉት።
ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት የኢትዮጵያ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ወንዶች ናቸው ሲልም ስታስቲካ አትቷል።
ፌስቡክ በጣም ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ ማህበራዊ የትስስር ገጽ ሲሆን፤ ባለቤቱ ሜታ ኩባንያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ማለትም የዋትስአፕ፣ ፌስቡክ ሜሴንጀር እና ኢንስታግራም ባለቤትም ነው።
ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ በዓለም ዙሪያ የኩባንያው ምርቶች ወደ ሦስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ሰዎች ወርሃዊ ተጠቃሚዎች አሏቸው።
ሁለት ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን የሚጠጉ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎች ያሉት ፌስቡክ፤ በዓለም ዙሪያ ቀዳሚውና በጣም ታዋቂ ማህበራዊ ሚዲያ ነው።