ወደ ከተሞቻቸው መጥተው ስለኖሩ ብቻ እስከ 50 ሺህ ዩሮ የሚከፍሉ ሀገራት
በነዋሪዎች ድርቅ የተመቱ ሰባት የአውሮፓ ከተሞች ለአንድ ግለሰብ ከ15 ሺህ ዩሮ በላይ በመክፈል ላይ ናቸው
የነዋሪነት ጉርሻ ያገኙ ሰዎች 10 ዓሜመት የመኖር ግዴታ ተጥሎባቸዋል
ወደ ከተሞቻቸው መጥተው ስለኖሩ ብቻ እስከ 50 ሺህ ዩሮ የሚከፍሉ ሀገራት፡፡
በርካታ የአውሮፓ እና እስያ ከተሞች ልጅ የመውለድ ምጣኔ ዝቅተኛ መሆኑን ተከትሎ የዜጎቻቸውን ቁጥር ለማብዛት የተለያዩ ማበረታቻዎችን በመስጠት ላይ ናቸው፡፡
ልጅ ለሚወልዱ ዜጎችም በአስር ሺህዎች ገንዘብ በጉርሻ መልክ ከመስጠት ጀምሮ ወለድ አልባ ብድር፣ ነጻ መኖሪያ ቤት መስጠት፣ የሰርግ ወጪን መሸፈን እና ሌሎችንም ማበረታቻዎች በመስጠት ላይ ናቸው፡፡
እነዚህ ሀገራት ይህ አልበቃ ብሏቸው አነስተኛ ነዋሪዎች ያለባቸው ከተሞች ዜጎች ወደነሱ እንዲመጡ እና እንዲኖሩ በማባበበል ላይ ናቸው፡፡
እንደ ዩሮ ኒውስ ዘገባ ከሆነ በርካታ የአውሮፓ ከተሞች ዜጎች ወደ ከተሞቻቸው መጥተው እንዲኖሩላቸው እስከ 50 ሺህ ዩሮ ድረስ የሚከፍሉ ሀገራት እንዳሉ ገልጿል፡፡
ጣልያን፣ስፔን፣ ስዊዘርላንድ እና ሌሎችም ጉርሻ የሚከፍሉ ሀገራት ሲሆኑ የከተሞቹን ዝርዝር እንደሚከተለው አቅርቧል፡፡
ሀገራቱ ማበረታቻውን ሀገራቸው በተጨማሪም ለውጭ ሀገራት ዜጎችም እድሉን እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡
የስዊዟ አልቢኔን ተራራማ ከተማ 250 ብቻ ነዋሪዎች ያሏት ሲሆን ተጨማሪ ህዝብ ወደ ከተማዋ ለማምጣት የተለያዩ ማበረታቻዎችን ዘርግታለች፡፡
ወደዚች ከተማ የሚመጣ ነዋሪ 50 ሺህ ዩሮ ጉርሻ የሚሰጠው ሲሆን ልጅ ይዞ ወደ ከተማዋ የሚመጣ ከሆነ ደግሞ በአንድ ህጻን 10 ሺህ ዩሮ ይከፈለዋል ተብሏል፡፡
ይህች ከተማ እድሉን የምትሰጠው ለስዊዘርላንድ ዜግነት ላላቸው እና የመኖሪያ ፈቃድ ላላቸው የውጭ ሀገር ዜገች ሲሆን እሉን ያገኘ ነዋሪ ቢያንስ 10 ዓመት የመኖር ግዴታ እንደተጣለበትም ተገልጿል፡፡
የስፔኗ ፖንጋ ገጠራማ ከተማ ደግሞ 600 ነዋሪዎች ብቻ ያሏት ሲሆን የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት አዲስ ለሚመጡ ነዋሪዎች 3 ሺህ ዶላር የሚሰጥ ሲሆን ልጅ ካለ ደግሞ በአንድ ህጻን 2 ሺህ 600 ዩሮ ይከፍላል፡፡
የጣልያኗ ካላብሪያ ደግሞ ሌላኛዋ በነዋሪዎች ድርቅ የተመታች ከተማ ስትሆን 2 ሺህ ነዋሪዎች ብቻ አሏት፡፡
ይህች ከተማ ለአዲስ ነዋሪዎች 28 ሺህ ዩሮ ትከፍላለች የተባለ ሲሆን 40 ዓመት እና ከዛ በላይ የሆናቸው ነዋሪዎች ከመጡላት በደስታ እንደምትቀበል ተገልጿል፡፤
ሌላኛዋ በደቡባዊ ጣከልያን የምትገኘው ፕሪሲስ አኩሪካ የተሰኘችው ገጠራማ ከተማ ደግሞ ወደ ግዛቷ ለመጡ አዲስ ነዋሪዎች 30 ሺህ ዩሮ ትከፍላለችም ተብሏል፡፡
ሳርዲኒያ የተባለችው የጣልያን የወደብ ከተማ ደግሞ የሕዝብ ብዛቷን ለማሳደግ ለአዲስ ነዋሪዎች እስከ 15 ሺህ ዩሮ እንደምትከፍል በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
የጣልያን መንግስት በሰው ድርቅ የተመቱ ከተሞችን ለመደጎም 45 ሚሊዮን ዩሮ በየዓመቱ እንደሚመድብም ተገልጿል፡፡