እስራኤል በጋዛ በየቀኑ ለ4 ሰዓታት ውጊያ ለማቆም መስማማቷን አሜሪካ አስታወቀች
የእስራኤል ጦር የውጊያ ማቆም ስምምነቱ ለሰብዓዊ ድጋፍ የተደረገ እንጂ ተኩሰ አቁም አይደልም ብሏል
ሃማስ ከእስራኤል ጋር እስካሁን ምንም አይነት ስምምነት አልደረስኩም ብሏል
እስራኤል በየቀኑ ለ4 ሰዓታት የሚቆይ ውጊያ የማቆም ስምምነት ላይ መድረሷን አሜሪካ አስታውቃለች።
እስራኤል ከስምምነቱ የደረሰችው ሰዎች ከጦርነት ቀጠና እንዲወጡ እና ሰብዓዊ ድጋ እንዲደረስ መንገድ ለመከፍት እንደሆነም ተነግሯል።
የአሜሪካ ነጩ ቤተ መንግስት ዋይተ ሃውስ እስራኤል የወደሰችውን እርምጃ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ሲል አድንቋል።
የአሜሪካ ብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጆን ኪብሪ፤ የመጀመሪያው የሰባዓዊ የውጊያ ማቆም ተግባር ከትናት ጀምሮ እንደሚተገበር አስታውቀዋል።
“የውጊያ ማቆም በሚተወጅበት ሰዓት በሰሜን ጋዛ እና አካባቢው ምንም አይነት ወተደራዊ እንቀስቃሴ እንደማይኖር ተነግሮናል” ብለዋል ቃል አቀባዩ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ምንም አይነት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዳልደረሰች ገልጻ፣ ነገር ግን ሰብዓዊ ርዳታ ለማድረግ ለአጭር ጊዜ ውጊያዎችን ልታቆም እንደመትትል ተናግራለች።
የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ሪቻርድ ሄክት “የተኩስ አቁም የለም፣ እደግመዋለሁ የተኩስ አቁም የለም፤ እኛ እያደረግን ያለነው፣ ያ የአራት ሰዓት መስኮት ታክቲካዊ እና ለሰባዓዊ ድጋፍ የሚደረግ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ከእስራኤል ጋር ውጊያ ላይ የሚገኘው የፍሊስጤሜ ሃማስም “ከእስራኤል ጋር እስካሁን ምንም አይነት ስምምነት አልደረስኩም” ብሏል።
የሃማስ መሪ ኢስማኢል ሃኒዬህ የፖለቲካ አማካሪ ታሄር አል-ኖኖ በታናንትናው ዕለት እንዳሉት ግልጽ ያልሆነ ድርድር እንደቀጠለ እና እስካሁን ከእስራኤል ጋር ምንም አይነት ስምምነት አልደረሰም ሲሉ ተናረዋል።
ሃማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ እና ያለተጠበቀ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው።
በሰሜን ጋዛ በእስራኤል ጦር እና በሃማስ ታጠቂዎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን፤ በተለይም በሰሜን ጋዛ በተለያዩ ግንባሮች ውጊያው ተጠናክሮ ቀጥሏል።