ይህ በዓል ከታህሳስ ሁለተኛ ሳምንት ጀምሮ በተለያዩ ሀገራት ይከበራል
የእየሱስ ክርስቶስን መወለድ ተከትሎ የገና በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ በደማቁ ይኩበራል።
ይህ በዓል እንደየሀገራቱ ባህልና ወግ መሰረት በታህሳስ ወር ከሁለተኛው ሳምንት ጀምሮ በተለያየ መንገድ የሚከበር ዓለም አቀፍ በዓል ነው።
በአሜሪካ እና በአውሮፓ የገና በዓል ከአዲስ ዓመት በዓላቸው ጋር አቀናጅተው በደማቁ ያከብሩታል። ብዙዎቹ ሀገራት በገና በዓል ዕለት መደበኛ ስራዎችን በመዝጋት በቤታቸው ተሰብስበው ያከብሩታል።
ይህ በዚህ እንዳለ ግን የገና በዓል ምን እንደሆነ እና በዓሉን ከነጭራሹ የማያከብሩ ሀገራት እንዳሉ ያውቁ ይሆን?
ቻይና የገና በዓልን ከማያከብሩ የዓለማችን ሀገራት መካከል ዋነኛዋ ስትሆን ዕለቱም እንደሌሎች የስራ ቀን ተብሎ ይውላል።
ቻይና በይፋ ሀይማኖት የሌላት ሀገር ስትሆን የገናን በዓል ማክበርም ህገወጥነት ነው ተብሏል።
አፍጋኒስታን ሌላኛዋ የገናን በዓል የማታከብር ሀገር ስትሆን አብዛኛው የሀገሪቱ ዜጎች ሙስሊሞች መሆናቸው ለበዓሉ አለመከበር ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።
አፍሪካዊቷ አልጀሪያ ሌላኛዋ የገና በዓል የማይከበርባት ሀገር ስትሆን በተለይም ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣችበት 1962 ጀምሮ የገናን በዓል አክብራ አታውቅም።
98 በመቶ የእስልምና እምነት ተከታዮች ህዝብ ያላት ኮሞሮስ የገናን በዓል የማታከብር ሌላኛዋ የዓለማችን ሀገር ናት።
ሊቢያ እና ሞሪታንያ የገና በዓል የማይከበርባቸው ተጨማሪ የአፍሪካ ሀገራት ሲሆኑ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች አለመኖር ደግሞ ለበዓሉ አለመከበር ዋነኛው ምክንያት ነው ተብሏል።
እስያዊቷ ሞንጎሊያ የገና በዓል የማይከበርባት ስትሆን የሀገሪቱ ዜጎች የቡድሂስት እምነት ተከታዮች ናቸው ተብሏል።
ሌላኛዋ የእየሱስ ክርስቶች ልደት ወይም ገና የማይከበርባት ሀገር አመጸኛዋ ሰሜን ኮሪያ ናት። በዚህ ሀገር የገናን በዓል ማክበር ለእስር እና ተጨማሪ ጉዳት እንደሚዳርግ በህግ መደንገጉ ተገልጿል።
ፓኪስታን ሌላኛዋ የዓለማችን ሀገር ስትሆን ዓለም በታህሳስ 25 በየዓመቱ የገናን በዓል ሲያከብር እሷ ግን የፓኪስታን መስራች የሚባሉትን መሀመድ አሊ ጅናህን አስባ ትውላለች።
ሳውዲ አረቢያ የገናን በዓል ማክበር የከለከለች ሀገር ስርሆን በዓሉን የሚያመለክት የገና ዛፍ እና ሌሎች መሰል ድርጊቶችን ማከናወን ለቅጣት ይዳርጋል ተብሏል።
ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ከፈረንጆቹ 2009 ጀምሮ የገና በዓል በሀገሯ እንዳይከበር በህግ ያገደች አፍሪካዊት ሀገር እንደሆነች ተገልጿል።
ታጃኪስታን፣ ቱኒዝያ፣ኡዝበኪስታን እና የመን የገና በዓል በሀገራቸው እንዳይከበር ህግ የደነገጉ ሀገራት ናቸው።