የመርሳት በሽታ ከፍተኛ የሆነባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
በፊንላንድ ከ1 ሺህ ሰዎች ውስጥ 56ቱ በመርሳት በሽታ ይጠቃሉ ተብሏል
የስራ ባህሪያቸው ከማስታወስ ጋር የተያያዙ ስራዎችን የሚሰሩ ሰዎች ለመርሳት በሽታ የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ እንደሆነ ተገልጿል
የመርሳት በሽታ ከፍተኛ የሆነባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
የመርሳት በሽታ የሰዎች አዕምሮ መታወክ ሲሆን ቀስ በቀስ ሰዎች የማስታወስ እና የማሳብ ችሎታቸውን ሲያጡ የሚከሰት ህመም እንደሆነ የህክምና ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡
ማስታወስ አለመቻል፣ የቋንቋ አጠቃቀም መለወጥ፣ የባህሪ ለውጦች፣ ጣዕሞችን ለመለየት መቸገር፣ ጥያቄዎችን መደጋገም፣ የተለመዱ ዕለታዊ ስራዎችን መስራት አለመቻል ወይም ቀላል ስራዎችን ለመስራት ረጅም ጊዜ መውሰድ ደግሞ ከበሽታው ምልክቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
እንደ ዓለም አቀፉ ስነ ህዝብ ጥናት ማዕከል መረጃ ከሆነ ፊንላንድ፣ዩናይትድ ኪንግደም፣ ስሎቫኪያ እና ኔዘርላንድ በአንጻራዊነት በመርሳት በሽታ የተጠቁ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ የሆነባቸው ሀገራት ናቸው፡፡
በመርሳት በሽታ የተጠቁ ዜጎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው የተባለ ሲሆን ለመድልዎ እና መገለል ይጋለጣሉ፡፡
ለዚህ ህመም ተጠቂዎች ተገቢው የሕክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳልሆነም የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ያስረዳል፡፡