የምግብ ብክነት የከፋባቸው የአፍሪካ ሀገራት
በዓለማችን በየዓመቱ አንድ ትሪሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ምግብ እንደሚባክን ጥናቶች ያሳያሉ

የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የምግብ ዕጥረት ካለባቸው ሀገራት መካከል ቀዳሚ ሆነዋል
የምግብ ብክነት የከፋባቸው የአፍሪካ ሀገራት
እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ሪፖርት ከሆነ በዓለማችን በየዓመቱ አንድ ትሪሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ምግብ ሳይበላ ይጣላል።
ወደ አፍሪካ ስንመጣ ደግሞ የምግብ ዕጥረት ያለባቸው ሀገራት መገኛ የሆነው ምስራቅ አፍሪካ ብክነቱ ከፍተኛ የሆኑ ሀገራት ይገኙበታል።
ታንዛንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሲሸልስ እና ሩዋንዳ የምግብ ብክነት ከፍየኛ ከሆነባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
በታንዛንያ 152 ኪሎ ግራም ምግብ በየዓመቱ ሲባክን በሩዋንዳ 141 ኪሎ ግራም ምግብ እንዲሁም በሲሸልስ 183 ኪሎግራም ምግብ እንደሚባክን በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል።
ናይጀሪያ ፣ ሞዛምቢክ እና ኡጋንዳም ከፍተኛ የምግብ ብክነት ያለባቸው ሀገራት ናቸውም ተብሏል።