በቤት ውስጥ የወንዶች ጥቃት የበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
በብዙ የዓለማችን ሀገራት የቤት ውስጥ ጥቃቶች በሴቶች ላይ ቢሆንም በተቃራኒው የሆነባቸው ሀገራትም አሉ

ከሰባት ወንዶች አንዱ በህይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ የቤት ውስጥ ጥቃት ይፈጸምበታል
በቤት ውስጥ የወንዶች ጥቃት የበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
መቀመጫውን በብሪታንያ ለንደን ያደረገው ማንካየንድ ኢንሺዬቲቭ የተሰኘው ተቋም ባወጣው ሪፖርት ከሆነ በቤት ውስጥ በወንዶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች በሚገባ ሪፖርት አይደረጉም፡፡
እንደ ተቋሙ ሪፖርት ከሆነ በዓለማችን ከሰባት ወንዶች አንዱ በህይወት ዘመኑ የቤት ውስጥ ጥቃት በፍቅረኛው አልያም በሚስቱ ቢያስ አንድ ጊዜ ይፈጸምበታል፡፡
የጥቃት መጠኑ በብሪታንያ እና አሜሪካ ከፍተኛ የሚባል ሲሆን ከሶስት ወንዶች መካከል አንዱ ለቤት ውስጥ ጥቃት የተጋለጠ ነው፡፡
ችግሩ መኖሩን የጠረዱ የተወሰኑ ሀገራት በተለይም ጀርመን እና ብሪታንያ የቤት ውስጥ ጥቃት ለተጋለጡ ወንዶች የጤና እና ስነ ልቦና ድጋፍ የሚያገኙባቸው ማዕከላትን አቋቁመዋል፡፡
ስዊድን እና ቻይናም በወንዶች ላይ የቤት ውስጥ ጥቃት ከበዛባቸው ሀገራት መካከል ሲጠቀሱ ከአፍሪካ ካሜሩን በአንጻራዊነት ጥቃቱ ከፍ ካለባቸው ሀገራት መካከል ተጠቅሳለች፡፡
ለቤት ውስጥ ጥቃት የተጋለጡ ወንዶች በሚደርስባቸው ጉዳት ምክንያት ራሳቸውን ለማጥፋት፣ ጭንቀት እና ድብርት እንደሚጋለጡ የተቋሙ ሪፖርት ላይ ተጠቅሷል፡፡