የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩከሬን ግንባር ጠንካራ ጥቃት እየሰነዘረ መሆኑን ኪቭ አስታወቀች
ሩሲያ ከሰላም ድርድሩ ቀድሞ ጦርነቱን ለመጨረስ የጥቃቱን ፍጥነትና ጥንካሬ ጨምራለች ተብሏል

የዩክሬን ጦር በምስራቅ በኩል ሩሲያ በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ 261 የውጊያዎች እንደከፈተች አስታውቋል
የሩስያ ወታደሮች በምስራቃዊ ዩክሬን የከፈቱት ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ አጠናክረው መቀጠላቸውን ኪቭ አስታወቀች።
የዩክሬን ጦር የፈረንጆቹ 2025 ከጀመረ ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ከባድ እና ጠንካራ ጥቃት እየተሰነዘረበት መሆኑን የገለፀ ሲሆን፤ ቅዳሜ እለት በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 261 የውጊያዎች እንደተከፈተበት አስታውቋል።
የሩሲያ ጦር ዋነኛው የጥቃት ኢላማ ቁልፍ የሉጂስቲክ ማእከል የሆነችው ፖክሮቭስክ ከተማ መሆኗመ ኪቭ አስውቃለች።
የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ እንደሚያመለክተው የሞስኮ ወታደሮች በ2024 አጋማሽ በምስራቅ ግንብር ቀስ በቀስ እየገፉ በርካታ ምንደሮችን መያዙን ይታወቃል።
የሩስያ ሃይሎች ከፖክሮቭስክ በስተደቡብ የሚገኘውን ግዛት የተቆጣጠሩ ሲሆን፤ አሁን ወደ ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ እየገፉ መሆኑም ነው የተነገረው።
የዩክሬን እና የሩሲያን ጦርት ለማቆም የሚያስችል ንግግር ለመጀመር እንቅስቀሴ ባለበት ሰዓት ነው ሩሲያ ጥቃቷን አጠናክራ የቀጠለችው።
የኔቶ ባለስልጣናት፤ “ሩሲያ ከሰላ ድርድሩ ቀድሙ ጦርነቱን ለመጨረስ የጥቃቱን ፍጥነትና ጥንካሬ ጨምራለች” ያሉ ሲሆን፤ ከዚህም የየበለጠ ከባድ እና ጠንካራ ውጊያዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም ገምተዋል።