በማሰብ አቅም (IQ) ቀዳሚ የሆኑ የዓለማችን ሀገራት
የእስያዎቹ ሲንጋፖር፣ ቻይና እና ደቡብ ኮሪያ ከቀዳሚዎቹ ሀገራት መካከል ናቸው

ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን እና ኬፕቨርዴ በአንጻራዊነት ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሀገራት ናቸው ተብሏል
በማሰብ አቅም (IQ) ቀዳሚ የሆኑ የዓለማችን ሀገራት
የማሰብ አቅም ሰዎች በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው እያጎለበቱት የሚሄድ ሲሆን በተለይም ችግር የመፍታት አቅም፣ አመክንዮ የማቅረብ አቅም እና የንግግር ክህሎቶችን በመመዘን የሚገኝ ነው፡፡
እውቀት ከሀገር መሰረተ ልማት እና ቴክኖሎጂ የመጠቀም አቅም ጋር የሚያያዝ በመሆኑ የተሻለ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸው የተሻለ የማሰብ አቅም ያላቸው ዜጎች ይኖሯቸዋል፡፡
ይህን ተከትሎም የዓለም ስነ ህዝብ ምልከታ ተቋም ባወጣው ሪፖርት መሰረት የእስያ ሀገራ የተሻለ የማሰብ አቅም እንዳላቸው በሪፖርቱ ላይ ጠቅሷል፡፡
ሲንጋፖር፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ሲይዙ ቤላሩስ፣ፊንላንድ እና ጀርመን ከአራተኛ እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
በዓለም የማሰብ አቅም ፈተናዎች ላይ አፍሪካዊን ሀገራት የማይሳተፉ በመሆናቸው የቅርብ ጊዜ መረጃ እንደሌለ በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡
197 የዓለማችን ሀገራት በተሳተፉበት የተቋሙ የ2017 የማሰብ አቅም ሪፖርት መሰረት ላይበሪያ፣ሴራሊዮን እና ኬፕቨርዴ የመጨረሻዎቹ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡