የቡድን 7 አባል ሀገራት የቻይናን ፕሮጀክት ለመከላከል በማሰብ 600 ቢሊዮን ዶላር ሊያሰባስቡ ነው
የአውሮፓ ህብረትም ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለመሰብሰብ ቃል ገብቷል
ቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ ከ100 በላይ በሆኑ ታዳጊ ሀገራት ውስጥ በሚገኙ መሰረተ ልማቶች ላይ ኢንቨስት የማድረግ እቅድ አላት
የቡድን ሰባት መሪዎች በእሁድ እለት ባደረጉት ስብሰባ በአምሰት አመት ውሰጥጠ 600 ቢሊዮን ዶላር ከግል እና ከመንግስት ለመሰብሰብ ቃል ገብተዋል።
ሀገራቱ ይህን የሰበሰቡት በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት አስፈላጊ የሆኑትን መሠረተ ልማቶችን ለመደገፍ እና የቻይናን የቆየ ባለ ብዙ ትሪሊዮን ዶላር የቤልት ኤንድ ሮድ ፕሮጄክት ለመከላከል ነው።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ሌሎች የቡድን ሰባት መሪዎች በዚህ አመት በደቡብ ጀርመን በሽሎስ ኤልማው በተካሄደው አመታዊ ስብሰባው አዲስ የተሰኘውን "ሽርክና ለአለምአቀፍ መሠረተ ልማት እና ኢንቨስትመንት" እንደገና አስጀምረዋል፡፡
አሜሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ እንዲሁም የዓለምን ጤና፣ የሥርዓተ-ፆታ ፍትሃዊነትን እና የዲጂታል መሠረተ ልማትን ለማሻሻል የሚረዱ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ 200 ቢሊዮን ዶላር በእርዳታ፣ በፌዴራል ፈንድ እና በግል ኢንቨስትመንት በአምስት ዓመታት ውስጥ እንደምታንቀሳቅስ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።
"ግልጽ መሆን እፈልጋለሁ። ይህ እርዳታ ወይም በጎ አድራጎት አይደለም፣ ለሁሉም ሰው የሚሆን ኢንቨስትመንት ነው" ብለዋል ባይደን፣ ሀገሮቹ "ከዴሞክራሲ ጋር በመተባበር የሚያገኙትን ተጨባጭ ጥቅም እንዲያዩ ያስችላቸዋል" ብሏል።
ባደን በመቶ ቢሊየን የሚቆጠር ተጨማሪ ዶላሮች ከመልቲላተራል ልማት ባንኮች፣ ከልማት ፋይናንስ ተቋማት፣ ሉዓላዊ የሀብት ፈንድ እና ሌሎችም ሊመጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
የአውሮፓ ህብረትም ለዚሁ ፕሮጀክት 300 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያሰባስብ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን ለተሰብሳቢው ተናግረዋል።
የቻይና የኢንቨስትመንት እቅድ ከኤዥያ ወደ አውሮፓ ያለውን ጥንታዊ የሐር መንገድ የንግድ መስመር ዘመናዊ ስሪት ለመፍጠር ያለመ እና ከ100 በላይ ባላይ በሚገኙ ሀገራት ወደብ፣ መንገድና ድልድይ ለመገንባት ነው፡፡
የዋይት ሀውስ ባለስልጣናት እቅዱ ለብዙ ታዳጊ ሀገራት ትንሽ ተጨባጭ ጥቅም አላስገኘም ብለዋል።
ባይደን በአንጎላ የ2 ቢሊዮን ዶላር የፀሐይ ልማት ፕሮጀክት ከንግድ ዲፓርትመንት፣ ከዩኤስ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ፣ ከአሜሪካ ኩባንያ አፍሪካ ግሎባል ሻፈር እና የአሜሪካ የፕሮጀክት ገንቢ ፀሐይ አፍሪካን ጨምሮ በርካታ ዋና
አሜሪካ ለአለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤአይዲ) በአምስት አመታት ውስጥ እስከ 50 ሚሊየን ዶላር ለአለም ባንክ አለም አቀፍ የህጻናት እንክብካቤ ማበረታቻ ፈንድ ትሰጣለች ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
የቡድን ሰባት ሀገራት ለልማት ዕርዳታ የሚሰጡት ከጠቅላላ ሀገራዊ ገቢያቸው 0.32 በመቶውን ብቻ ሲሆን ይህም ቃል ከተገባው 0.7 ከመቶ ከግማሽ በታች የሚሆነውን ነው ትላለች።