በኢትዮጵያ አማካይ የእድሜ ጣሪያው ስንት አመት ነው?
በ2023 በአለም አቀፍ ደረጃ አማካይ የእድሜ ጣሪያው 70.8 አመት እንደሚሆን የመንግስታቱ ድርጅት ገልጿል
በኢትዮጵያ ያለው አማካይ የእድሜ ጣሪያ ከአለም አቀፉ አማካይ በሶስት አመት ዝቅ ያለ ነው
የመንግስታቱ ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በ2023 በአለም አቀፍ ደረጃ በህይወት የመቆያ እድሜ 70.8 አመት እንደሚሆን ተተንብዩዋል።
አማካይ የእድሜ ጣሪያው ከሀገር ሀገር ከከተማ ከተማ የሚለያይ ሲሆን፥ኢትዮጵያ በ67.81 አመት ከ193 ሀገራት 149ኛ ደረጃን ይዛለች።