በህይወት ያሉ የእድሜ ባለጸጋ ተብለው ህጋዊ እውቅና የተሰጣቸው የ113 አመት አዛውንቱ ቬንዙዌላዊ ዩዋን ቪሴንት ፔሬዝ ናቸው
“የአለማችን የእድሜ ባለጸጋ” እንደሆኑ በቤተሰቦቻቸው የሚነገርላቸው የመናዊ ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ።
አሊ አንተር የተባሉት አዛውንት በ140 አመታቸው ባለፈው ሳምንት ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸውን ዋቢ ያደረገው ሚረር ዘግቧል።
አሊ እድሜያቸው በትክክል ተረጋግጦ እውቅና ባይሰጣቸውም በየመን ረጅም አመቱ የኖሩ አዛውንት መሆናቸው ይነገራል።
እድሜያቸው መቶን ሲደፍን በቀኝም በግራም ጭንቅላታቸው በኩል ቀንድም መሳይ ነገር ያበቀሉት አሊ፥ እስከ 2017 ድረስ የማስታወስም ሆነ አጠቃላይ ጤናቸው መልካም እንደነበር ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል።
- አንደኛውን የአለም ጦርነት የሚያስታውሱት ፈረንሳዊት በ118 አመታቸው አረፉ
- ደቡብ አፍሪካዊቷ የ128 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ ረጅም እድሜ የመኖራቸውን ሚስጢር ተናግረዋል
ከግንባራቸው ከፍ ብለው የወጡት ነገሮች እያደጉ ወደ ጉንጫቸው መውረድ ሲጀምሩ ግን ጤናቸው እክል ገጥሞታል።
እነዚህ ቀንድ መሳይ ነገሮችም የእድሜ ባለጸጋውን “ቀንዶ” የሚል የፌዝ ስም አሰጥቷቸው ቤተሰቦቻቸውም ለአመታት ተሳቀው ቆይተው ከሰሞኑ የወሰዱት እርምጃ ለህልፈት ሳያበቃቸው እንዳልቀረ ተገልጿል።
በህክምና ተቋም በቀዶ ህክምና መወገድ የነበረባቸው የበቀሉት ነገሮች በፍም እሳት በጋለ ብረት እንዲወገዱ ከተደረገ ከሶስት ቀናት በኋላ ነው አሊ አንተር ያረፉት።
ይህን ያደረጉት የቅርብ ቤተሰቦቻቸው አዛውንቱ ከእድሜ መግፋት ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ማለፉን ቢገልጹም አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ ዘመድ ግን “እጅግ ኋላቀር በሆነ መንገድ ቀንዶቹን ለማስወገድ የተደረገው ጥረት” አሊን ለከባድ ህመም ዳርጓቸው ህይወታቸው ማለፉን ተናግሯል።
የየመኑ ኤደን አል ጋሃድ ጋዜጣ እንዳስነበበው አሊ አንተር ከ70 በላይ ልጅና የልጅ ልጆች ነበሯቸው።
በአለማችን በህይወት ያሉ የእድሜ ባለጸጋ (ወንድ) ተብለው ህጋዊ እውቅና የተሰጣቸው የ113 አመት አዛውንቱ ቬንዙዌላዊ ዩዋን ቪሴንት ፔሬዝ መሆናቸው ይታወቃል።