በዋና ከተማቸው የሚጠሩ የዓለማችን ሀገራት
በዓለማችን ካሉ ሀገራት መካከል 11 ሀገራ የሀገራቱ እና ዋና ከተማቸው ተመሳሳይ ነው

ጅቡቲ፣ ኩዌት እና ሜክሲኮ ደግሞ በዋና ከተማቸው ከሚጠሩ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
በዋና ከተማቸው የሚጠሩ የዓለማችን ሀገራት
በዓለማችን 193 ሀገራት በይፋ የሀገርነት እውቅና ያገኙ ሀገራት ሲኖሩ ከነዚህ ውስጥ 11ዱ ዋና ከተማቸው እና የሀገራቸው ስም ተመሳሳይ ነው፡፡
በአፍሪካ ካሉ 54 ሀገራት መካከል ምስራቅ አፍሪካዊቷ ጅቡቲ ዋና ከተማዋ እና የሀገር ስሟ ተመሳሳይ መጠሪያን በብቸኝነት ትከተላለች፡፡
ከመካለኛው ምስራቅ ደግሞ በነዳጅ የበለጸገችው ኩዌት በተመሳሳይ በዋና ከተማዋ የምትጠራ ሀገር ተብላለች፡፡
የላቲን አሜሪካዎቹ ሜክሲኮ እና ጓቲማላ በዋና ከተማቸው ከሚጠሩ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ሲሆኑ ሉግዘምበርግ፣ አንዶራ እና ሳን ማሪኖ ከአውሮፓ በተመሳሳይ በዋና ከተማቸው የሚጠሩ ሀገራት ናቸው፡፡
የእስያ ኢንዱስትሪ መዲናዋ ሲንጋፖር በተመሳሳይ በዋና ከተማዋ የምትጠራ ሀገር ተብላለች፡፡