ሩሲያ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ፈጣን የተባለውን ግስጋሴ እያደረገች ዩክሬን ግዛቶች እየተቆጣጠረች ነው
ሩሲያ በዛሬው እለት የተለያዩ የዩክሬን ከተሞችን ክሩዝ ሚሳዔል ተጠቅማ መደብደቧ ተሰምቷል።
ሩሲያ በክሩዝ ሚሳዔል ድብደባ ከፈጸመችባቸው ከተሞች መካከልም ኦዴሳ፣ ክሮፒቭኒትስኪ፣ ካርኪቭ፣ ሪቪን እንዲሁም ሉትስክ እንደሚገኙበት የዩክሬኖቹ ዘርካ እና ሰስፕላይ የሄና ምንጮች አስታውቀዋል።
የዩክሬን የኢነርጂ ሚኒስተር ሄርን ሁለስቼንኮ በጉዳዩ ዙሪያ በፌስቡክ ገጻቸው ባጋሩት መረጃ፣ “በጠላት መጠነ ሰፊ ጥቃት የኃይል መሰረተ ልማች በድጋሚ ኢላማ ተደርገዋል” ብለዋል።
“ጠላት የካርኪቭ ከተማን በሚሳዔል ማጥቃቱን ቀጥሏል” በማለት የከተማዋ ከንቲባ በቴሌገራም ባሩት ጽሁፍ የሩሲያን የክሩዝ ሚሰዔል ጥቃት አረጋግጠዋል።
ሩሲያ የዩክሬን ከተሞችን በክሩዝ ሚሳዔሎች የደበደበችው ዛሬ ጠዋት ሲሆን፤ ምን ያክል ሚሳዔሎችን እንደተኮሰች እና ያስከተለው የጉዳት መጠን እሳካሁን ድረስ ይፋ አልተደረገም።
ዩሩሲያ ክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ያሳለፈነው ሳምንት የነበረው ክስተት ግጭቱ ወደ ከፍተኛ ሁኔታ መሸጋሩ የታየበት ነበር።
ጦርነቱ እንደ አዲስ ያገረሸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዩክሬን የአሜሪካ የረጅም ርቀት ሚሳዔሎችን ተጠቅማ የሩሲያ ግዛት ውስጥ ጥቃት እንደትፈጽም መፍቀዳቸውን ተከትሎ ነው።
ሞስኮ ዩክሬንን በአዲስ የመካከለኛ ርቀት ባሊስቲክ መሳሪያ ስትመታ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ አስደንግጦ ተጨማሪ ስጋትን ከፍ በማድረግ የሩሲያ ዩክሬን የሚዔል ፍጥጫውን ትንሽ ረገብ አድርጎታል።
ይሁን እንጂ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የገጠመችው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ፈጣን የተባለውን ግስጋሴ እያደረገች ዩክሬን ግዛቶች እየተቆጣጠረች መሆኑን የዘርፉ ተንታኞች ይናገራሉ።
የሩሲያ ጦር ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 235 ካሬ ኪ.ሜ የዩክሬንን መሬት ተቆጣጥሯል የተባለ ሲሆን፤ ይህም የፈረንጆቹ 2024 አዲስ ክብረወሰን ነው።
ሩሲያ እየተገባደደ ባለው የፈረንጆቹ ህዳር ወር ብቻ 600 ካሬ ኪ.ሜ የዩክሬንን መሬት መቆጣጠሯንም ዲፕ ስቴት የተባለውን እና ለዩክሬን ጦር ቅርበት ያለውን ተቋም ዋቢ በማድረግም የወጣ መረጃ ያመለክታል።