
ዙሪክ ፣ኒውዮርክ እና ሲንጋፖር ደግሞ ኑሮ ውድ የሆነባቸው የዓለማችን ከተሞች ተብለዋል
ኑሮ ርካሽ የሆነባቸው የዓለማችን 10 ከተሞች
ቢዝነስ ኢንሳይደር ዓለም አቀፉን የኢኮኖሚክ ኢንተለጀንስ ዩኒትን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ የሶሪያዋ ደማስቆ በአንጻራዊነት ኑሮ ያልተወደደባት ከተማ ሆናለች።
ሸማቾች ለኑሮ አስፈላጊ የሚባሉ ሸቀጦችን በቀላሉ መግዛት ይችላሉ የተባለ ሲሆን የኢራኗ ቴህራንም ሁለተኛዋ ከተማ ተብላለች።
ተቋሙ የዋጋ ጥናቱን የሰራው የየሀገራቱ መገበያያ ገንዘብ የመግዛት አቅም፣ የከተማዋ ነዋሪ ብዛት ፣የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ፣ የከተማዋ ቆዳ ስፋት እና የሸቀጦች አማካይ ዋጋን ከግምት ውስጥ ማስገባቱን አስታውቋል።
173 የዓለማችን ከተሞች በተሳተፉበት በዚህ ጥናት መሰረትም የሊቢያዋ ትሪፖሊ፣ የህንዷ ቼናይ፣ የኡዝቤኪስታኗ ታሽኬንት እና የዛምቢያዋ ሉሳካ በአንጻራዊነት የሸቀጦች ዋጋ ርካሽ መሆኑ ተገልጿል።
የስዊዘርላንዷ ዙሪክ፣ ኒውዮርክ እና ሲንጋፖር ደግሞ ለመኖር ውድ የሆኑ ከተሞች እንደሆኑ ተገልጿል