ኢኮኖሚ
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪን በመጠቀም ቀዳሚ የሆኑ የአውሮፓ እነማን ናቸው?
የአውሮፓ ህብረት ከ10 ዓመት በኋላ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች አግዳለሁ ብሏል
ጀርመን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ቀዳሚዋ የአውሮፓ ሀገር ተብላለች
የዓለማችን ሀብታሙ አህጉር አውሮፓ ከፈረንጆቹ 2035 ጀምሮ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በአውሮፓ ጎዳናዎች እንዳይጓዙ አደርጋለሁ ብሏል።
ለዚህ እቅድ እንዲረዳቸውም የህብረቱ አባል ሀገራት ከወዲሁ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ላይ ናቸው።
አሁን ባለው መረጃ መሰረት ጀርመን 1 ሚሊዮን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ያሏት ሲሆን የአራት ሀገራት ህብረት የሆነችው ዩናይትድ ኪንግደም (ብሪታንያ) 641 ሺህ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች አሏት።
ፈረንሳይ በ605 ሺህ እንዲሁም ኖርዌይ በ603 ሺህ ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃን ይዘዋል ተብሏል።
በርካታ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ያላቸውን ሀገራት ይመልከቱ፦