የዓለም ቁንጅና ውድድሮችን ደጋግመው ያሸነፉ ሀገራት እነማን ናቸው?
ሚስ ወርልድ በመባል የሚታወቀው የቁንጅና ውድድር ከ1952 ጀምሮ እእየተካሄደ ይገኛል
ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ላይ በዲና ፈቃዱ አማካኝነት አንድ ጊዜ ብቻ ተወዳድራ በምርጥ 20 ቆነጃጅት ዝርዝር ውስጥ ተካታ ነበር
የምድራችን ቆንጆ ወይም "ሚስ ዩንቨርስ" በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፉ የቁንጅና ውድድር ከፈረንጆቹ 1950ዎቹ ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ይህን ውድድር አሜሪካዊያ ቆነጃጅት ዘጠኝ ጊዜ በማሸነፍ ቀዳሚ ሀገር ስትሆን የደቡብ አሜሪካዋ ቬንዙዌላ ቆነጃጅት ደግሞ ሰባት ጊዜ እንዳሸነፉ ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው በድረገጹ አስፍሯል።
ሌላኛዋ የሰሜን አሜሪካ ሀገር ፑሪቶ ሪኮ ቆነጃጅት ደግሞ አምስት ጊዜ እንዲሁም የእስያዋ ፊሊፒንስ አራት ጊዜ በማሸነፍ ተዘርዝረዋል።
ውድድሩን ከአፍሪካ የደቡብ አፍሪካ ቆነጃጅት በታሪክ ሶስት ጊዜ ያሸነፉ ተብለው ተመዝግበዋል።
ከአፍሪካ ከደቡብ አፍሪካ በተጨማሪ አንጎላ፣ ናሚቢያ እና ቦትስዋና ቆነጃጅት "ሚስ ዩንቨርስ"ን አንድ ጊዜ ያሸነፉ ሀገራት ናቸው።
ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2004 እስከ 2017 ድረስ በዚህ ውድር ላይ የሚሳተፉ ቆነጃጅትን ስትመርጥ የቆየች ቢሆንም በውድድሩ ላይ ግን አንድ ጊዜ ብቻ ተወክላለች፡፡
ዲና ፍቃዱ በፈረንጆቹ 2006 ላይ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ በተካሄደው የሚስ ዩንቨርስ 2006 ውድድር ላይ ኢትዮጵያን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወክላ የተሳተፈች ቢሆንም በምርጥ 20 ቆነጃጅት ውስጥ መካተት ችላም ነበር፡፡
ከዚህ ዓመት በኋላ እስከ 2017 ድረስ ኢትዮጵያን በሚስ ዩንቨርስ የቁንጅና ውድድር ላይ የሚወክሉ ቆነጃጅትን በየዓመቱ በውድድር ቢመረጡም ከዲና ፍቃዱ ውጪ ቀሪዎቹ በውድድሩ ላይ አልቀረቡም፡፡
ኢትዮጵያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚስ ዩንቨርስ ውድድር ላይ ለመካፈል ባቀደችበት በፈረንጆቹ 2004 ላይ ፍሬህይወት አበበ መኩሪያ በአዲስ አበባ በተካሄደው የቆነጃጅት ውድድር ላይ በአንደኝነት የተመረጠች ቢሆንም በውድድሩ ላይ ሳትካፈል ቀርታለች፡፡
ከ2018 ጀምሮም እስከ 2023 ድረስ በተካሄደው የሚስ ዩንቨርስ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን የሚወክል ቆንጆ መምረጥ ባለመቻሉ ምክንያት መሳተፍ አልተቻለም፡፡