ቼካዊቷ የዓለም የቁንጅና ውድድር አሸናፊ ሆነች
ፒይዝኮቫ ዘውድ የደፋችው የሊባኖሷን ያስሚና ዘይቶን፣ የትሪንዳድ እና ቶቤጎዋን አቼ አብራሀምን እና የቦትስዋናዋን ሌስጎ ቾምቦን በማሸነፍ ነው
የቼክ ሪፐብሊኳ ክርስቲና ፒይዝኮቫ ከመላው አለም የተውጣጡ 111 ቆነጃጅችን በመብለጥ የ2ዐ24 'ሚስ ወርልድ' ወድድርን በማሸነፍ ዘውድ ደፍታለች
የቼክ ሪፐብሊኳ ክርስቲና ፒይዝኮቫ ከመላው አለም የተውጣጡ 111 ቆነጃጅቶችን በመብለጥ የ2ዐ24 'ሚስ ወርልድ' ወድድርን በማሸነፍ ዘውድ ደፍታለች።
ውድድር በህንዷ ሙምባይ ከተማ በትናንትናው እለት ነበር የተካሄደው።
የውድድሩ አዘጋጅ ቡድን የመጨረሻው ውድድር ከመጀመሩ በፊት እንዳስታወቀው ቀደም ብለው በተካሄዱ ተከታታይ የማጣሪያ ውድድሮች በአካል ብቃት፣ በቁንጅና፣ በተሰጥኦ እና ህዝብ ፊት በመናገር እና በሌሎች በበርካታ መስፈርቶች 40 የሚሆኑ ተመርጠዋል።
ከ40ዎቹ ተወዳዳሪዎች 12ቱ መለየታቸውን እና ከ12 የተመረጡት ስምንቱ ደግሞ በቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባኤ መወያያ ርእሶች ዙሪያ በጥያቄ እና መልስ ውድድር እንዲሳተፉ ተደርገዋል።
የሴቶች ጤና ላይ ተጵዕኖ ስለሚያሳድር ጉዳይ እንድታብራራ የተጠየቀችው የ23 አመቷ ሞዴል እና የህግ ተማሪ ፒይዝኮቫ የወር አበባም ነውር ማድረግ መወገድ አለበት፤ "ሴቶ መሆን ስጦታ ነው" ስለሆነም የወር አበባ የነውር ርዕስ መሆኑ ማብቃት አለበት በማለት አብራርታለች።
በመጨረሻው የማጣሪያ ውድድር የቀሩት አራቱ በተለያዩ ርዕሶች ላይ ሀሳባቸውን በመድረክ አቅርበዋል። እነዚህ አራቱ የመጨረሻው ተወዳዳሪዎች እያንዳንዳቸው አፍሪካን፣ አሜሪካን፣ ከካሪቢያን፣ እስያን፣ ኦሽኒያን እና አውሮፓን የወከሉ ነበሩ።
ፒይዝኮቫ ዘውድ የደፋችው የሊባኖሷን ያስሚና ዘይቶን፣ የትሪንዳድ እና ቶቤጎዋን አቼ አብራሀምን እና የቦትስዋናዋን ሌስጎ ቾምቦን በማሸነፍ ነው።እነዚህ ቆነጃጅቶች የእንግሊዟን ጀሲካ ጋጀንን ጨምሮ በአህጉር ደረጃ አሸናፊ ናቸው።
"ቢኪኒ ኮንቴስት" በመባል በ1951 የተጀመረው በዩናይትድ ኪንግደም የተቋቋመው የዓለም የቁንጅና ውድድር ወይም ሚስ ወርልድ በዓለም ረጅም እድም ያስቆጠረ የቁንጅና ውድድር ነው።
በዚህ ውድድር ከፍተኛ እውቅና አትርፈዋል የሚባሉት አሸናፊዎች ሁለቱም ህንዳውያን ናቸው።
አንጀኛዋ የ1994ቱ ውድድር አሸናፊ አሽዋሪያ ራይ ባችቻን ስትሆን ሁለተኛዋ ደግሞ የውድድሩ 2000 አሸናፊ ፕሪያንካ ቾፕራ ጆናስ ነች።
ፒይዝኮቫ በ2022 ኃላፊነቷን የለቀቀችውን የፖላንድ ዜጋ የሆነችውን የዓለም ሞዴል ካሮሊና ቤልዋስካን ትተካለች።
የሚስ ወርልድ ውድድር በ2023 አልተካሄደም።