12 ጊዜ ተጋብተው የተፋቱት ባልና ሚስት
ባልና ሚስቶቹ በ43 ዓመታት ውስጥ 12 ጊዜ ተጋብተው ተፋተዋል
የኦስትሪያ ዜግነት ያላቸው እነዚህ ባልና ሚስት በመጨረሻም ፖሊስ ጉዳዩን እንደሚመረምር ገልጿል
12 ጊዜ ተጋብተው የተፋቱት ባልና ሚስት
ስማቸው ያልተጠቀሰው አንድ ኦስትራሊያዊት በቬና ከተማ የምትኖር ሲሆን ባለፉት 43 ዓመታት ውስጥ 12 ጊዜ ትዳር መስርታ 12 ጊዜ ተፋታለች፡፡
ከባለቤቷ ጋር ብትኖርበት መንደር ውስጥ ከባሏ ጋር ያላት ህይወት ብዙዎች የሚቀኑበት አይነት ነበር፡፡
ኦስትሪያ ከትዳራቸው ለሚፋቱ ሴቶች የህግ እና የኢኮኖሚ ድጋፍ ገንዘብ እንዲከፈላቸው የሚፈቅድ ህግ ያላት ሲሆን ህች ሴትም ከትዳሯ በተፋታች ቁጥር ገንዘብ ሲከፈላት ቆይቷል፡፡
ሀገሪቱ ሴቶች ከትዳራቸው ሲፋቱ ለህግ እና ሌሎች ድጋፎች በሚል 28 ሺህ ዶላር ትከፍላለች፡፡
ይሁንና በቅርቡ ከትዳሬ ተፋትቻለሁ በሚል የገንዘብ ድጋፉ እንዲከፈላት ባመለከትችበት ወቅት ተቋሙ ክፍያውን እንደማይፈጽም ይናገራል፡፡
ይህን ተከትሎ በተደረገ ማጣራት ሴትዮዋ ገንዘቡን ለማግኘት በሚል ከባሏ ጋር በተደጋጋሚ እንደምትፋታ እና መልሳ እንደምታገባ ይደረስባታል፡፡
ባልና ሚስቶቹ ተጋብተው በተፋቱ ቁጥር በድምሩ 341 ሺህ ዶላር ከመንግስት የተከፈላቸው ሲሆን ጉዳዩ ትኩረት ስቧል፡፡
የባልና ሚስቶቹ ጎረቤቶች እንደተናገሩት ጥንዶቹ ከመጋባታቸው ውጪ መፋታታቸውን እንደማያውቁ ለፖሊስ መናገራቸው ተገልጿል፡፡
ሚትየዋ የሀገሪቱ መንግስት ሴቶችን ለመርዳት በሚል የተዘጋጀውን ህግ ለራሷ እና ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት አውላለች የሚል ቅጣት ይጠብቃታል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡