በርካታ መፈንቅለ መንግስት የተካሄደባቸው ሀገራት
መፈንቅለ መንግስት የሚበዛው በምዕራብ ይሁን እንጅ በተሞከረ እና በተሳካ መፈንቅለ መንግስት ብዛት ሱዳን ቀዳሚ ሆናለች
በአፍሪካ በተለይም አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጡባቸው ከፈረንጆቹ 1950ዎቹ ወዲህ በርካታ መፈንቅለ መንግስታት ተካሂደዋል
በአፍሪካ በተለይም አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጡባቸው ከፈረንጆቹ 1950ዎቹ ወዲህ በርካታ መፈንቅለ መንግስታት ተካሂደዋል።
ከተካሄዱት መፈንቅለ መንግስት ጥቂቶቹ የተሳኩ ሲሆን አብዛኞቹ መክሸፋቸውን ቪኦኤ'መፈንቅለ መንግስት በአፍሪካ' በሚል ርዕስ ከአመት በፊት ያወጣው ዘገባ ያመለክታል።
መፈንቅለ መንግስት ከተካሄደባቸው ሀገራት ቀዳሚዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ናቸው።
ቡርኪናፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር በርካታ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራዎች የተካሄዱባቸው የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት መሆናቸው እሙን ነው።
መፈንቅለ መንግስት የሚበዛው በምዕራብ ይሁን እንጅ በተሞከረ እና በተሳካ መፈንቅለ መንግስት ብዛት ሱዳን ቀዳሚ ሆናለች።
ከ1950ዎቹ ጀምሮ በአፍሪካ ከተካሄዱ 214 የመፈንቅለ መንግስት ሙከራዎች ውስጥ 108 የሚሆኑ አልተሳኩም። 106 የመፈንቅለ መንግስት ሙከራዎች ግን ስኬታማዎች ነበሩ።
እንደ ቪኦኤ ዘገባ በአፍሪካ ከሚገኙ 54 ሀገራት ውስጥ 45 ቢያንስ አንድ ጊዜ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አጋጥሟቸዋል።
መልካም ያልሆነ አስዳደር፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና ራስወዳድነት እና ስግብግብነት መፈንቅለ መንግስት እንዲከሰት ምክንያት ይሆናሉ ተብለው ተጠቅሰዋል።